የባህል ስፖርቶች ውድድር ነገ በሃዋሳ ይጀመራል፤ መልካም እድል ለሲዴ ተወዳዳሪዎች!
ፎቶ ከ https://www.google.com.pe/url?sa=i&rct=j&q=&esrc=s&source=images&cd=&cad=rja&uact=8&docid=BrtdZFEjwpXJaM&tbnid=T_rvmxNsoecT6M:&ved=0CAQQjB0&url=http%3A%2F%2Fwww.skyscrapercity.com%2Fshowthread.php%3Ft%3D849248%26page%3D4&ei=CGh3U-fqB-irsQTVpICIAg&bvm=bv.66917471,d.aWw&psig=AFQjCNGDgRaNwr-ojorHu46ItlwzfrDbIw&ust=1400420733937651 አዲስ አበባ ግንቦት 9/2006 12ኛው የመላው ኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ነገ በሃዋሳ ይጀመራል። የኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው ውድድሩ ከነገ ግንቦት 10 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2006 ዓም ድረስ ይካሄዳል። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ከበደ ደስታ እንደተናገሩት በውድድሩ አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች በዘጠኝ የውድድር አይነቶች ይሳተፋሉ። የባህል ስፖርት ውድድሩ አርሶና አርብቶ አደሩን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ከፍል የሚሳተፍበት ይሆናል። ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ እንዲፈጸም ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። ለ10 ቀናት በሚቆየው በዚህ ውድድርና ፌስቲቫል ላይ ከአንድ ሺህ በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ። በየክልሎቹ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባህል፣ የቋንቋና የታሪክ ልውውጥ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል። የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር አቶ መዘረዲን ሁሴን በበኩላቸው በሀዋሳ በሚካሄደው የባህል ስፖርቶች ውድ