በአዲስ አበባ ዙሪያ ገበሬዎች የሚፈናቀሉት ያለ በቂ ዝግጅት ነው ተባለ፤ ተመሳሳይ እድል ለገጠማቸው የሃዋሳ ዙሪያ ገበሬዎችስ ምን ታስቦል?
የመሬት ወረራ መስመር ሰሜን፦ዳቶ ኦዳሄ ሰሞኑን ኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ እንዳስነበበው በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ ኣርሶ ኣደሮች ያለ በቂ ዝግጅት በተለያዩ ምክንያቶች ከመሬት ይዞታቸው የሚፈናቀሉ ሲሆን፤ ተፈናቃዮቹም ለተለያዩ ችግሮች በመጋለጥ ላይ መሆናቸውን ኣትቷል። በተመሳሳይም ልክ እንደ ኣዲስ ኣበባ ዙሪያ ገበሬዎች የሃዋሳ ዙሪያ ኣርሶ ኣደሮችም ለላፉት 20 ኣመታት ተመሳሳይ ከመሬት ይዞታቸው በተለያዩ ምክንያቶች የመፈናቀል እድል ገጥሞቸዋል። የመሬት ወረራ መስመር ምስራቅ፦ ጫፌ ( ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ ) እነዚሁ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው ባሻገር የኣገር ሽክም በመሆን ላይ ናቸው። መንግስት ይህን መሰል ያለ በቂ ዝግጅት የምደረግ የኣርሶ ኣደር የማፈናቀል ተግባራ ለመግታት ምን እያደረገ ነው? ለማንኛውም ስለ ሃዋሳ ዙሪያ ተፈናቃይ ኣርሶ ኣደሮች በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፤ ለኣሁኑ ግን ስለ ኣዲስ ኣበባ ዙሪያ ገበሬዎች ከታች ያንቡ፦ የመሬት ወረራ መስመር ደቡብ፦ ሎቄ ከግማሽ ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ካሣ የተከፈላቸው ገበሬዎች አሉ በተከፈላቸው ካሣ ንድግ ጀምረው የተሳካላቸው ጥቂቶች ናቸው “ቦታው ለሪል እስቴትና ለልማት ይፈለጋል ተብለን የእርሻ መሬታችንና የመኖሪያ ቦታችን በመንግስት ከተወሰደብን አራት አመታት ሞላን” ይላሉ - በሰበታ አዋስ ወረዳ እያረሱ ይኖሩ እንደነበር የገለፁ አርሶአደሮች፡፡ ለእርሻ መሬት እንደየስፋቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ የተከፈላቸው ገበሬዎች መኖራቸው አይካድም፡፡ ለመኖሪያ ቤትም 24 ሺ ብር ድረስ ካሳ እንደተከፈላቸውና ቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጥም ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር የተፈናቀሉ ገበሬዎች ያስታውሳሉ፡፡ “ከዛሬ ነገ ቦታ ተሰጥቶን ባለችን ብ