በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ ስታዲየም ዩኒቨርሲቲውን የሚያስተዋውቅና የማህበረሰብ አገልግሎትን የሚያጠናክር ማዕከል መሆኑ ተገለጸ
Photo from H.University website: Edited by Worancha Information Network በሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፤ በአንድ ጣሪያ ስር ሁሉን-አቀፍ አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል መልኩ እየተገነባ ያለው ስታዲየም፤ ተማሪዎች በዙሪያው ባሉ መዝናኛ ማዕከላት ተጠቅመው የሚዝናኑበትና ትምህርታቸውንም ሊያጠኑ የሚችሉበት ማዕከል መሆኑን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ዴቭሎኘመንት ምክትል ኘሬዚዳንት ኘ/ር ንጋቱ ረጋሳ ገለፁ፡፡ የስታዲየሙ መገንባት ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ዓመታት ወዲህ ለስፖርቱ ዕድገት የሰጠው ትኩረት ማሳያ ነው ያሉት ኘ/ር ንጋቱ፤ በከተማው የሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶችን በማስተናገድ ረገድ ምቹ አማራጭ ሊሆን እንደሚችልና ጎን ለጎንም ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢውን ለማሳደግና የአከባቢውን ማህበረሰብ ለማገልገል የሚያመርታቸውን ምርቶች የሚያቀርብባቸው ሱቆች በስታዲየሙ ዲዛይን ውስጥ መካተታቸው ማዕከሉ ለየት ያለ ኮምኘሌክስ ያደረርገዋል ብለዋል፡፡ በስፖርት ሳይንስ የተካኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት በትጋት እየሰራ ላለው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፤ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን የታመነበት ይህ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ኮምኘሌክስ፤ ለአከባቢው የስፖርት ቡድኖችም የመወዳደሪያና የልምምድ አማራጭ በመሆን ዩኒቨርሲቲው የማህብረሰብ አገልግሎትን የበለጠ እንደሚያጠናክር የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ ለግንባታው 140 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ኘ/ር ንጋቱ አስረድተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ኘሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስክያጅ የሆኑት አቶ ደንበሹ ነኤሬ በበኩላቸው የስታዲየሙን ግንባታ በማስመልከት በሰጡት ገለጻ¿ ዩኒቨርሲቲው በ2002 ዓ.ም የመንግስት ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎችን ስፖርት ውድድር ለማዘጋጀት አምስት ሺህ