የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 2ኛውን የኦፕን ዶር(Open-Door) ቀን አከበረ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በጋር በመሆን ሁለተኛውን የኦፕን ዶር ቀን በደመቀ ሁኔታ ሚያዝያ 14/2006 ዓ.ም አከበሩ፡፡ "የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን በመወከል ዶ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ የመክፈቻ ንግግር አድረገዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት ኦፕን ዶር በሀገራችን ብዙም ያተለመደ ነገር ግን የተለያዩ የምርምርና የቴክሎጂ ውጤቶችን የምናስተዋውቅበት ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታዎች አሉት ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍቅሬ አክለውም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እምርታና ለውጥ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲው ከአውሮፓ ከካናዳ እና አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በበኩላቸው እንዳተናገሩት መድረኩ በዩኒቨርሲቲውና እና በኢንስዲስትሪው መካከል ከፍተኛ ትስስር የሚፈጠርበትና ኢንስቲትዩቱ የሚሰራቸውን ስራዎች የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሞልቶት አክለው ይህ ቀን እንዲከበር በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች ዩኒቨርሲቲውን የደገፈው የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮን አመስግነዋል፡፡ ለግማሽ ቀን በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ማዕከል በተካሄደው መድረክ በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የትምርት ክፍሎችና ት/ት ቤቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባርና እንቅስቃሴ አስተዋውቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል የመወያያ ሰነድ በዶ/ር ሞልቶት ዘውዴ ቀርቧል፡፡ ውይይቱንም የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት