የሕዝብ ተሳትፎ በተግባር ይረጋገጥ!
ሪፖርተር ጋዜጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ ጄኔቭ ባዘጋጀው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግምገማ ላይ ኢትዮጵያ እየተገመገመች ነበር፡፡ በዚሀ ግምገማ ላይ ሦስት አገሮች ማለትም ናሚቢያ፣ ካዛክስታንና ቼክ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ በአቻ ገምጋሚነት ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ይህ በተመድ የተዘጋጀ ግምገማ ለሰብዓዊ መብት አከባበር የሕዝብ በአገር ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ተሳታፊ መሆን ዋነኛውና መሠረታዊው መርህ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በዚህ ግምገማ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትም የአንድ አገር ልማትና ዕድገት የሚረጋገጠው በሕዝብ ያልተገደበ ተሳትፎ ላይ ሲመሠረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይ በግምገማው ላይ ከተለያዩ አገሮችና ወገኖች የተነሱ መሠረታዊ የሚባሉት ነጥቦች ማለት የምንፈልጋቸውን በይበልጥ ያብራሩልናል፡፡ በተለይ አንኳር ተብለው የተነሱ ጉዳዮችን ስንመረምር የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊነትን ቁልጭ አድርገው ያስቀምጡልናል፡፡ በግምገማው ላይ ከተነሱ ሐሳቦች መካከል በ2007 ዓ.ም. ሊደረግ የታሰበው ብሔራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሁሉንም የሚያሳትፍ መሆን እንዳለበት፣ ኢትዮጵያ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በድጋሚ ማጤን እንደሚገባት፣ የጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲከኞች በዘፈቀደ መታሰርና መጉላላት መቆም እንዳለበት፣ ሕጋዊ አካሄድን የጠበቀ የዳኝነትና የፍትሕ ሥርዓት መኖር አስፈላጊ መሆኑን፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ላይ የወጣው ሕግ መሻሻል እንደሚኖርበት፣ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብርን ሙሉ ለሙሉ