የወንዶ ገነት ወረዳ የላብኣደሮችን ቀን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የወረዳው ነዋሪዎች የኣልባሳት ድጋፍ ኣደረገ።
የወንዶ ገነት ወረዳ የላብኣደሮችን ቀን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የወረዳው ነዋሪዎች የኣልባሳት ድጋፍ ኣደረገ። ድጋፍ የተደረገው ሰሞኑን የወረዳው ኣስተዳደር ባዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ ሲሆን፤ የወረዳው ድርግት በዞኑ ለሚገኙት ለሌሎች ወረዳ ኣስተዳደሮች ኣርኣያ ነው ተብሏል። በስነስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው ቁጥራቸው 300 ለሚሆኑት የኢኮኖሚ ችግርተኞች የኣልባሳት ድጋፍ የተደረገው የወረዳውን ባለሃብቶች እና የሃይማኖት ተቋማንት በማስተባበር በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው።