በዩኒቨርስቲዎች በተነሳው ተቃውሞ በርካቶች ሞቱ
የከፋ ጉዳት የደረሰው በአምቦ፣መደወላቦ እና ሐረማያ ነው ተቃውሞው እስከ ሃሙስ በመንግስት ሚዲያ አልተነገረም አዲስ አበባንና በዙሪያዋ የኦሮሚያ ከተሞችን በማካተት የተዘጋጀውን የጋራ ማስተር ፕላን የሚያወግዙ የክልሉ ተማሪዎች፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲያካሂዱት በሰነበቱት ተቃውሞ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፋ፡፡ በትንሹ ወደ መቶ የሚጠጉ ሰዎችም እንደቆሰሉና ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ በተቃውሞዎቹ ዙሪያ ቀጥተኛ ዘገባ ሲያስተላልፍ የነበረው የመንግስት ሚዲያ ሐሙስ እለት ከመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት የወጣውን መግለጫ ያቀረበ ሲሆን በአምቦና በመደወላቡ 3 ተማሪዎችን ጨምሮ 7 ሰዎች እንደሞቱ አትቷል፡፡ ሲኤንኤንና ሌሎች የሚዲያ ተቋማት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን በመጥቀስ የተለያዩ ዘገባዎችን ያሰራጩ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ 30 ሰው መሞቱን እንደተናገሩ ጠቅሰዋል፡፡ የእግር ኳስ ጨዋታ በቴሌቭዥን የሚመለከቱ የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ፈንጂ አንድ ተማሪ እንደሞተና 70 ሰዎች እንደቆሰሉም መግለጫው አስታውሶ፤ ዩኒቨርስቲዎች እንደተረጋጉ መንግስት ቢገልፅም በስልክ ያነጋገርናቸው የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ግን ግጭቱና ውጥረቱ እንዳልበረደ ተናግረዋል፡፡ በአዳማ፣ በጅማ፣ ሃሮማያ፣ አምቦ፣ ነቀምት፣ መደወላቡ እና ድሬደዋ ዩኒቨርሲዎች በተነሳው ተቃውሞ እስካሁን ከተገለጸው በላይ የሞትና የአካል ጉዳት በተማሪዎች ላይ እንደደረሰ የየአካባቢው ምንጮች የገለፁ ሲሂን፣ በርካቶች እንደታሰሩም ጠቁመዋል፡፡ በሃሮማያ ፍንዳታ የሞቱት ተማሪዎች ሁለት መሆናቸውን የገለፁ ምንጮች፣ በብሄር ተወላጅነት የተቧደኑ ተማሪዎች ጎራ ለይተው በፈጠሩት ግጭት በርካታ ተማሪዎች እንደተደባደቡ ተናግረዋል፡፡ አዲስ