“...ክፍተቱን ማጥበብ ትልቅ ነገር ነው...”
“...ክፍተቱን ማጥበብ ትልቅ ነገር ነው...” የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (WATCH) ዋች ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትና እናቶች ዙሪያ አፋጣኝና መሰረታዊ የሆኑ ሕክምናዎችን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና በተለያዩ መስተዳድር አካላት ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ስልጠና አስቀድሞ በየመስ ተዳድር አካላቱ የሚገኙ የዞን ...የወረዳ... አካላት እና ሌሎች መሰል ተቋማት ውስጥ በኃላፊነት የሚሰሩ አባላትን ስለጉዳዩ በቂ እውቀት እንዲያገኙ ከጤና ባለሙያዎቹ አስቀድሞ ስልጠና ሰጥቶአል፡፡ ከስልጠናው በሁዋላ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? በሚል በደቡብ ብሔር ብሔረ ሰቦች ሐዋሳ ዙሪያ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ ለዚህ እትም ንባብ እነሆ ብለናል፡፡ ...አንድ አባት ከመኪና ውስጥ አጠገቤ ተቀምጠዋል። በምናልፍበት አካባቢ ከርቀት አንድ ጤና ጣብያ ተመለከትን፡፡ የምንመለከተው ጤና ጣቢያ ማን ይባላል? አልኩና ጠየቅ ሁዋቸው፡፡ እሳቸውም እኔም ለአገሩ እንግዳ ስለሆንኩ አላውቀውም የሚል ነበር መል ሳቸው፡፡ ቀጠል አድርገውም ...ምን...ጤና ጣብያ በየቦታው ተሰርቶ እያለ ነገር ግን ተጠ ቃሚው በተለይም እናቶች እምብዛም ናቸው... ብዙዎቹ የሚወልዱትም በቤታቸው ነው ...አሉኝ፡፡ ለምንድነው ብዬ ስጠይቅ ...ይህንን እኔም አላውቅም...እራሳቸውን ብታገኝ ያቸው እና ብትጠይቂ ጥሩ ነው አሉኝ ...እና ተለያየን፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ብሄረሰቦች ዘንድ የተለያዩ ጎጂና ጎጂ ያልሆኑ ልማዳዊ ድርጊች እንደነበሩ እና አልፎ አልፎም አሁንም እንደሚፈጸሙ እሙን ነው፡፡ አንዲት የሲዳማ ሴት እንዳወጋችን ከሆነ... “...በደቡብ ሲዳማ አካባቢ ሐሜሳ የሚባል ከእንጨት መሰል