የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን እያወዛገበ ነው፤ የሃዋሳውስ?
ሰሞኑን የኣዲስ ኣበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን እያወዛገበ መሆኑን ተሰምቷን። የጋራ ማስተር ፕላኑ በኦሮሚያ የፖለትካ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን በክልሉ ገዥ ፓርቲ ኣባላት ጭምር ድጋፍ ተነግፎታል። ለመሆኑ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር እና ሲዳማ ዞን ምን ኣስበው ይሁን ? ዞሮ ዞሮ እነርሱም ወደ ጋራ ማስተር ፕላን መግባታቸው ኣይቀርምእና። ለማንኛውም የኣዲስኣበባው እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወዝግብ ከታች ያንቡ፦ ተቃዋሚዎች የጋራ ፕላኑን ተቃወሙ ዕቅዱ የአዲስ አበባን የመሬት ችግር ለመፍታት እንጂ ለልማት አይደለም - (ኦፌኮ) አዲስ አበባንና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችን በልማት ለማስተሳሰር ላለፉት ሁለት ዓመታት ጥናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ የተቀናጀ የጋራ ልማቱን ለመተግበር የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ባለፈው ሳምንት በአዳማ በተካሄደ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ለውይይት ቀርቦ ነበር፡፡ የአዲስ አበባንና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችን የ10 ዓመትና 25 ዓመት የልማት ዕቅዶች የያዘው የጋራ ማስተር ፕላን የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችና ስጋቶችን የቀሰቀሰ ሲሆን ህገ መንግስታዊ ጥያቄም አስነስቷል፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ዞን እስካሁን የአዲስ አበባ ቆሻሻ መጣያ ሆኖ እንደቆየ የጠቀሱት አንድ የውይይቱ ተሳታፊ፤ አንድ ከተማ ዕቅድና ፕላን ይዞ ሲነሳ የራሱ ፖሊሲ አይኖረውም ወይ?” ሲሉ ጠይቀው “አንዱ ተቀባይ አንዱ ሰጪ ሆኖ እስከመቼ ይዘለቃል? ብለዋል፡፡ ልዩ ዞኑ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደመኖሩ ጨፌ ኦሮሚያ በዞኑ ላይ የመወሰን ስልጣን አለው የገለፁት እኚሁ ተናጋሪ፤ ጨፌ ኦሮምያ በጉዳዩ ላይ ሳይወያይና ሳይወስን ወደ ተግባር ከተገባ ስልጣን መጋፋት አይሆንም ወይ?” በማለት አስረግጠው ጠይቀዋል፡፡ ሌላው አስተያየት ሠጪ በበ