ደቡብ ግሎባል ባንክ ወደ አትራፊነት መግባቱን ገለጸ
- የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ግዥ ፈጸመ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለመሰማራት ይጠየቅ የነበረውን የተከፈለ 100 ሚሊዮን ብር ወደ 500 ሚሊዮን ብር ከማሳደጉ በፊት 15ኛው የግል ባንክ በመሆን የአገሪቱን የባንክ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ደቡብ ግሎባል ባንክ 19 ወራት አስቆጥሯል፡፡ ከሌሎች የግል ባንኮች በተለየ በአንድ የአክሲዮን ሽያጭ ፕሮግራም በሚሊዮን የሚቆጠር አክሲዮን በመሸጥ በ138.9 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በማሰባሰብ ወደ ሥራ የገባ ባንክ ነው፡፡ በ5481 ባለአክሲዮኖች የተመሠረተው ይህ ባንክ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ በመጀመርያው የሥራ ዓመት (10 ወራት) አትራፊ መሆን ባይችልም በአሁኑ ወቅት ግን ወደአትራፊነት እየገባ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡ የባንኩን የ19 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ በተሰጠ መግለጫ ላይ እንደተመለከተው፣ ባንኩ መጋቢት 2006 ዓ.ም. 14.5 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ እንደገለጹት፣ በመጀመርያው ዓመት ላይ ተመዝግቦ የነበረው ኪሳራ አሁን መለወጡንና በየወሩ እያተረፈ መጓዝ ጀምሯል፡፡ በመጀመርያው የሥራ ዘመንም ትርፍ ይገኛል ተብሎ ባይጠበቅም ደቡብ ግሎባል ባንክ ግን በአጭር ጊዜ ወደ ትርፍ መግባት ከመቻሉም በላይ አሁን እያስመዘገበ ያለው ትርፍ በ2006 በጀት መዝጊያ ጥሩ ትርፍ የሚያገኝ መሆኑን ያሳያልም ብለዋል፡፡ በመጋቢት 2006 ዓ.ም. ያስመዘገበው የትርፍ መጠንም አምና ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 223 በመቶ ብልጫ ያለው ነው፡፡ ባንኩ ትርፍ ማስመዝገብ ከመጀመሩ ባሻገር በዋና ዋና የባንክ አገልግሎቱ እያደገ መምጣቱን የፕሬዚዳንቱ ገለጻ ያስረዳል፡፡ የባንኩ የሥራ እንቅስቃሴ በለውጥ ጎዳና ላይ ስለመሆኑም ዋና