ይታሰብበት!
ከዘረፋ ያልዳነው ሀዋሳ ከተማና እና እድለኛ ያልሆነው የሲዳማ ቡና ክለብ ከማህበራዊ መረብ ከ ላይ የተገኘ በ Hagerselam Haroressa ስለሀዋሳ ስነሳ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ውበት ብቻ አይደለም የሚነሳው፡፡ ተፈጥሮ የለገሰቻትን ውበት ምክንያት በማድረግ በህጋዊ መንገድ ወደ ከተማይቱ ከምተመው ኢትዮጵያዊ ህዝብ በላቄ መልኩ በህገ ወጥ መንገድ ሾልኮ በመግባት ከተማይቱንና የአካባቢውን ህብረተሰብ እረፍት የሚነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እያሻቀበ መተዋል፡፡ ለዚህ የመንግሥት አካላት በተለይም የከተማው ማዘጋጃ ጽ/ቤት እና ከንቲባው ጽ/ቤት ይህ ነው የሚባል የማስተካከል እርምጃ ስወስዱ አይታዩም፡፡ ይልቁንም ከሌቦች ጋር በመተባበር የከተማውን ወረራ ያፋጥናሉ እንጂ፡፡ አሁን ደግሞ በያዝነው ሳምንት ተመሳሳይ የዘረፋ ተግባር በሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና እሱን ከላይ ሆኖ ከሚቆጣጠሩት እራሳቸውን መርጦ ባለሥልጣን የሆኑ አካላት የ ከተማይቱን የዘረፋ ሂደት እየተፋፋሜ ነው የሚል ነገር በስፋት ይነገራል፡፡ የከተማሞችን ”አዲሱ ሊዝ አዋጅ” ህብረተሰቡን ለወጉ እንኳን ሳያወያይ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ የንግድና የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የማግኘት እድል መካከለኛ ገቢ ላለው ማኅበረሰብ ክፍል በተለይም ለጭቁኑ መንግስት ሰራተኛ ዝግ በማድረግ እየተሻረከና እየነገደ ያለው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ34 ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ተጫዋቾች በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ቦታ ጀባ ማለቱ ተሰምተዋል፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ደረጃ ለሚገኙ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ተጫዋቾች መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ተወስኖ የነበረ ቢሆንም የከተማ አስተዳደር ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ብሩ ወልደ ለ