ኢትዮጵያና ኬንያን ከሚያገናኘው የሐዋሳ ሞያሌ መንገድ የተወሰነው ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ኢትዮጵያና ኬንያን ሚያገናኘው የሐዋሳ ሞያሌ የመንገድ ፕሮጀክት የተወሰነው በመጠናቀቀቅ ላይ ነው። በአጠቃላይ የአዋሳ ሞያሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በ5 ነጥብ 3 ቢሊዮን የሚገነባ ሲሆን ፥ ስድስት ተቋራጮችም እየተሳተፉበት ይገኛል ። የሀዋሳ-ሞያሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በየብስ ለማገናኘት እየተገነቡ ካሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው። ለአብነትም ለመንገዱ አምስተኛ ክፍል የሆነው የያቤሎ ሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ ከሃገረ ማሪያም እስከ ያቤሎ ያለው የመንገዱ አራተኛ ክፍልም በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። ሌሎቹ የመንገዱ ክፍሎች በዚህ ዓመት ግንባታቸው የተጀመሩ ሲሆን ፥ በቀጣዩ ዓመት የሚጀመሩም እንዳሉ ነው በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ የሚናገሩት ። የፕሮጀክቶቹ የጊዜ መራራቅ የተከሰተው በተቋራጮች በቶሎ ወደ ስራ አለመግባት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሳምሶን ፥ 186 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሀዋሳ-ሀገረ ማርያም መንገድም ለሶስት ተቋራጮች ተከፍሎ በዚህ ዓመት ግንባታው መጀመሩን ገልፀዋል ። ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኘውና በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የመንገዱ የመጨረሻ ክፍልም በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ግንባታው የሚጀመር ሲሆን ፥ ሙሉ መንገዱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባም የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሃላፊው ገልፀዋል ። ኢትዮጵያም ለኬንያ ከምትልካቸው ምርቶቿ የምታገኘው ገቢ ዝቅተኛ የሚባል የነበረና በአንፃሩ ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ ካላት ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ያለው አናሳ መሆኑ ነው የሚነገ