Posts

ሲዳማ ባለፈው ሳምንት፦ ኬጂ ቻን በቦርቻ

Image
ፎቶ ሮፖርተር ጋዜጣ ታዋቂው የሆሊውድ አክተር ኬጂ ቻን ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ልማት ድርጅት (ፋኦ) ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ተዋናዩ ፋኦ በደቡብ ክልል ያሉትን ፕሮጀክቶች ተዘዋውሮ ጐብኝቷል፡፡  ከጉብኝቱ መልስ ዓርብ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ቻን እንደገለጸው፣ ጉብኝቱ የግብርና ባለሙያዎችን፣ ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ለመመልከትና ከሚኒስትሮች ጋር ለመወያየት ዕድል ሰጥቶታል፡፡ ከጉብኝቱ በፊት ስለ ኢትዮጵያ የነበረው ዕውቀት በእውን ካለው የተለየ እንደነበር የገለጸው ቻን፣ የአጭር ጊዜ ዕርዳታ ከመስጠት በዘለለ ዘለቄታ ያለው ዕርዳታ ማቅረብ እንደሚገባው የተማረበት እንደሆነ ተናግሯል፡፡  ጄኪ ቻን በተለያዩ የዕርዳታ ሰጪ ቡድኖች የሚንቀሳቀስ ሲሆን ይህን ለየት የሚያደርገው ከ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ጋር በተያያዘ በተለይም ረሀብን ለማጥፋትና ሰላምን በዓለም ለማስፈን ጥሪ የሚያቀርብበት መሆኑ ነው፡፡ ለቻን 60ኛ ዓመት ልደት ከሃምሳ በላይ አገሮች የተወጣጡ ሙዚቀኞች ይሳተፉበታል የተባለ የሙዚቃ ኮንሰርት በቤጂንግ የሚካሄድ ሲሆን ‹‹ፒስ ኤንድ ላቭ›› (ሰላምና ፍቅር) በሚል የዕርዳታ ማሰባሰቢያም ይሆናል፡፡ በዕለቱ ተዋናዩ የሰው ልጅ እርስ በርስ በፍቅርና በሰላም ይኖር ዘንድ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን ‹‹ተፈጥሮአዊ አደጋ በሞላበት የሰው ልጅ ሰቆቃ በተንሰራፋበት ዓለም ሰው ሠራሽ ችግር በላይ በላዩ አይጨመር፤ ሁላችንም በሰላም እንኑር፤›› የሚል መልዕክቱን አድርሷል፡፡  ሐዋሳ ላይ በኃይሌ ሪዞርት ልደቱን አስመልክቶ የተጋበዘው ቻን በጉብኝቱ ወቅት በተለይ በኢትዮጵያ ባህላዊ እስክስታ በመደመም፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ

NEWS ALERT: Jackie Chan to Visit Hawassa and Boricha Wereda

Image
The Hong Kong native Hollywood film star, Jackie Chan, is to visit Ethiopia for two days, arriving here in Addis on Thursday, March 20, 2014, the Food & Agricultural Organization (FAO) disclosed today. Known for his acrobatic fighting style, with a bit of comic timing, Chan is invited by FAO to visit one of its programmes in Hawassa, 276Km south of Addis Abeba. Copied from Brazil, FAO has Purchase from Africans for Africa (PAA), a programme that buys cereals and vegetables from smallholder farmers to supply feeding programmes made to schools. FAO and the World Food Programme (WFP) jointly run PAA in Boricha Wereda of the Southern Regional State, targeting 2,000 farmers. WFP distributes the food bought through this programme to 8,000 students in seven primary schools. Chan, to be received by Tefera Deribew, minister of Agriculture, and Modibo Traore (PhD), sub-regional coordinator of FAO in East Africa, at Bole International Airport tomorrow, will meet some of the 1,334 stud

Sidama and Ethiopian

Image
Sidama and Ethiopian :  the emergence of the Mekane Yesus Church in Sidama Abstract (en)  : The present work belongs to local African church history and international mission history.The author shows why and how the Sidama people in south Ethiopia became part of theevangelical movement. During the last hundred years this group has experienced a lot ofchanges, incorporated in the greater Ethiopia, being influenced by the internationalmissionary movement, occupied by an European power and becoming a part of themodernising movement. As a result of all the changes and impulses the people faced, the Sidama to a great extendturned away from their traditional worldview and practices including their religion andaccepted the Christian Evangelical faith. The origin and the development that led to the foundation of the Ethiopian EvangelicalChurch Mekane Yesus in Sidama are described, as part of the local church history. Theauthor wants to underline how political, social and cultu

ክትባት ለህጻናት እና እናቶች በሲዳማ

Image
ሀዋሳ መጋቢት 10/2006 በሲዳማ ዞን የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የምዕተ ዓመቱን የጤና ልማት ግብ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡ በዞኑ በላፉት ስድስት ወራት ከ318 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የተለያየ የበሽታ መከላከያ ክትባት ሲሰጥ ከ274 ሺህ የሚበልጡ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለልጆቻቸው የሚሰጠው ክትባት ህፃናት ከበሽታ በመጠበቅ ጤናቸው የተሻለ እንዲሆን እንደረዳቸው እናቶች ገልፀዋል፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አበበ በካዬ እንደገለጹት የእናቶችና ህፃናትን የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የምዕተዓመቱን የጤና ልማት ግብ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ ነው፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ሁሉም ህፃናት ክትባት እንዲወስዱ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በ19 ወረዳና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች 318 ሺህ 715 ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት የፖሊዮ፣ የቲቪ፣ የኩፍኝና የሳንባ ምች በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ ለህፃናት ሞት ምክንያት የሆነው የሳምባ ምች መከላከያ ክትባት በመደበኛ የክትባት አገልግሎት ውስጥ በማካተት 107 ሺህ 751 ህፃናት መከተባቸውን አስታውቀዋል፡፡ በወሊድ እድሜ ክልል ለ274ሺህ ሴቶች ይርጋዓለም ሆስፒታልን ጨምሮ ከ650 በሚበልጡ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች የስነ ተዋልዶና ቤተሰብ ምጣኔ የአገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮ እቴነሽ ጋላናና ወይዘሮ አልማዝ ወርቁ ለህፃናት በሚሰጠው የበሽታ መከላከያ ክትባት ህፃናት ከበሽታ

በሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከመልካም ተሞክሮ ባሻገር ጥቃቅን ችግሮችም አይናቁ

Image
ወደ ሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ስዘልቅ ሞቃታማ አየሯን የምትረጨውን ፀሐይ ተቋቁመው በየትምህርት መስካቸው ተግባራዊ ልምምድ የሚያደርጉ ተማሪዎች እዚህም እዚያም ሲታትሩ ታይተውኛል። በስተቀኝ በመንገድ ሥራ የሚሠለጥኑ ተማሪዎች አፈሩን እየደለደሉና እየጠቀጠቁ ጥራት ያለው መንገድ እንዴት መሥራት እንደሚቻል ተግባራዊ ልምምድ ሲያደርጉ፤ በስተግራ ደግሞ በኮብል ስቶን ሥራ እና በቅየሳ የሚሠለጥኑ ተማሪዎች በየሙያቸው የሚያስፈልጓቸውን ቁሶች ታጥቀው ሙሉ ትኩረታቸውን በልምምዱ ላይ አድርገው ይታያሉ። ከተማሪዎቹ መካከል ወደ አንዱ ጠጋ ብዬ  « ሥልጠና እንዴት ነው ?»  የሚለውን የጋዜጠኛ ጥያቄዬን አስቀደምኩ። ተማሪው አራርሶ ወልዴ ይባላል። የመጣው ከሀዲያ ዞን ሾኔ ከሚባል አካባቢ ነው። የሦስተኛ ዓመት የመንገድ ሲቪል ዎርከ ሠልጣኝ ሲሆን፤ በኮሌጁ በነበረው ቆይታ በክፍተትና በመልካም ተሞክሮነት የሚጠቀሱ ጉዳዮችን እንዲህ በማለት ይገልጽልኝ ጀመር  «  ባለፉት ዓመታት የመምህራን እጥረት ነበር። በሳምንት አምስት ቀን መማር ቢኖርብንም አንዳንድ ቀን መምህራን እየጠፉ ትምህርት የማናገኝበት ቀን ነበር። ይሁን እንጂ ያሉት መምህራን ጊዜያቸውን በመሰዋት ትምህርት እየሰጡን ክፍተቱን ለመሙላት ይጥሩ ነበር። አንዳንድ ለተማሪ ፍቅር የማይሰጡ መምህራንም ነበሩ። ተማሪ ሊያጠፋ ይችላል መምህር መቻል፣ መምከርና ትምህርቱን በአግባቡ መስጠት መቻል አለበት።  » ሠልጣኝ አራርሶ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ሰባ ከመቶ ተግባር ተኮር እንዲሆኑ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሚሰጠው ሥልጠና በኮሌጃቸው በአግባቡ እየተተገበረ መሆኑን ይናገራል። ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን ሥልጠና በክፍል ከተማሩ በኋላ ቀሪውን በተግባር ይሰለጥናሉ። በእነርሱ የሥልጠና ዘርፍ የተሟሉ የተግባር ት