የግብፅ ሚኒስትር የግድቡ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ ተቋረጠ
የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ በጠየቁት መሠረት ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ቢገቡም፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ በሰዓታት ውስጥ ተቋረጠ፡፡ የግብፅ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑና ከባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ሰኞ መገናኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ተያያዥ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከጋዜጠኞች ጋር ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙት አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የግብፅ አቻቸው ሁለት አጀንዳዎችን ይዘው መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ የግብፅ ሚኒስትር በስልክ ደውለው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣትና ለመወያየት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መገኘታቸውንና ይዘው የመጡዋቸው አጀንዳዎችም ከዚህ ቀደም ተቀባይነት ሊያገኝ ያልቻለውን የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተጨማሪ ጥናት እንዲያከናውን የሚጠይቅ፣ እንዲሁም በግንባታው ላይ መተማመንን ማጐልበት የሚሉ ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድንን በተመለከተ ኢትዮጵያና ሱዳን እንደማይቀበሉት ከዚህ ቀደም መገለጹንና አሁንም ይህንን አቋም በድጋሚ እንዲገነዘቡት መደረጉን አቶ አለማየሁ አስረድተዋል፡፡ በግድቡ ግንባታ ላይ መተማመንን ማጐልበት በሚል በግብፅ በኩል በቀረበው ሐሳብ ውስጥ የቀድሞው የግብፅ የውኃ መጠን እንደማይቀንስ ኢትዮጵያ እንድታረጋግጥ የሚጠይቅ መሆኑን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ በሰኞው ስብሰባ የግብፁ ሚኒስትር በድጋሚ አንስተው ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ግልጽ እንደተደረገላቸው አቶ አለማየሁ በ