Posts

የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለብ በዞኑ መንግስት ትኩረት ተነፍጓል ተባለ

Image
ከሲዳማ ዞን መንግስት ትኩረት የተነፈገው የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለቡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር ያለ ውጤት ጉዞውን ቀጥሏል። ሲዳማን በወከል በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ካሉት የእግር ኳስ ክለቦች መካከል የይርጋዓለም ከተማ ተወካይ የሆነው ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሽንፈትን ማስተናገዱን ቀጥሏል። እስከኣሁን ደረስ ካደረጋቸው ኣስር ጫዋታዎች መካከል ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል ጋር የደረገውን  ጫዋታ ከማሸነፉ ሌላ በተቀሩት በስድስት ጫዋታዎች በመሸነፍ እና በሁለቱ ብቻ ነጥብ በመጋራት በደረጃ ሰንጠረ ዥ ኣስራ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ይገ ኛ ል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን የክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞ  የሲዳማ ዞን መንግስትን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኣካላት ትኩረት በ መነፈጉ የተነሳ መሆኑን ኣንዳንድ የክለቡ ደጋፊዎች ተናግረዋል ። በጉዳዩ  ዙሪያ ሪፖርተራችን ቱንስሳ ጂሎ በይርጋኣለም ከተማ ያናገራቸው የክለቡ ደጋፊዎች እንደምሉ ት ከሆነ ፤ የሲዳማ ክለቦች ያልሆኑትን እንደወላይታ ዲቻ ያሉትን በቅርብ በፕሪሜዬር ሊግ ውድድር የገቡ ክለቦችን በገንዘብ እና በሰው ኃይል ለማጠናከር በሲዳማ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲረዱ ለሲዳማ ክ ለ ቦች ግን መሰል ዝግጅቶችን ኣልተደረጉም ። ክለቡ ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም እና በፋይናስ ኣቅሙን በማጠናከር ውጤታማ ለማድረግ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ስለሌሉ ክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞውን ለመቀጠል ተገዷል ብለዋል። ኣክለውም፤ ክለቡ ያሉበትን የብቃት ችግሮች ኣስተካክሎ በቀጣይ ውድድሮች ማሸነፍ ካልቻለ ከፕሪሜዬር ሊግ ውድድር መውረዱ ስለማይቀር የሚመለከታቸው ኣካላት ክለቡን በሰው እና ፋይናንስ ኃይል የ

Patient satisfaction with outpatient health services in Hawassa University Teaching Hospital, Southern Ethiopia

Image
ለተጨማሪ ንባብ ፦ Full Length Research Paper

Fish Market at Awassa Lake

Image
ተጨማሪ  ፎቶዎችን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ፦  Fish Market at Awassa Lake

AWASSA KENEMA VS. KEDUS GIORGIS

Image

የይርጋለም ከተማ የንጽህ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት መቼ ይሁን የምጠናቀቀው?

Image
ኣንድ ሚሊዮን ለምጠጉ የ ይርጋለም ከተማ እና ለኣከባቢዋ የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች ኣገልግሎት ይሰጣል ተብሎ፤ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው የውሃ ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች ከሚጠበቀው በላይ ተጓቷል። ይህ የውሃ ፕሮጀክት 60  ሊትር በሰከንድ ወይም  5  ሺ  142  ሜትር ኪዩብ በቀን የመስጠት አቅም ያለው እና እስከ  2012 ዓ . ም ድረስ ለ 898  ሺ ያህል የከተማዋ ሕዝብ አገልግሎት ለመሥጠት ያስችላል መባሉ ይታወሳል ። እንደ ኣዲስዘመን ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ፤ የውሃ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ከቧንቧ መገጣጠሚያ አካል  ( ፊቲንግ )  አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ መጓተቱን የሥራ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡ አምስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ካሉት ፕሮጀክት መካከል ሁለቱ በጄነሬተር ሥራ ቢያስጀምሩም ሌሎቹ ግን ውሃ መስጠት አልቻሉም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ውሃ መግፋት የሚያስችል በቂ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት ነው።   « ትራንስፎርመር ለማስተከል ክፍያ የፈፀምነው በ 2003  ዓ . ም ቢሆንም እስካሁን ከአንዱ በቀር ምላሽ አልተሰጠንም »  የሚሉት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች፤ በዚህ ምክንያት ህብረተሰቡ በቂ ውሃ ማግኘት አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ትራንስፎርመር ቢተከልም በሶስት ቀን ውስጥ እንደፈነዳና አገልግሎት እንዳቆመ ይናገራሉ፡፡ የፈነዳውን ለማስለወጥ ያደረጉት ጥረት ምላሽ አለማግኘቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ፤ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ የገበያና ሽያጭ ኃላፊ አቶ ታደሰ መርጋ፤ ከፍላጎት መጨመር ጋር ተያይዞ ወረፋ መኖሩን ገልፀው፤  « ፈነዳ »  ስለተባለው ትራንስፎርመር ግን የሚያውቁ