Posts

የሕፃናት ሽያጭና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽን ፀደቀ

Image
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና የሕፃናትን የወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽንን ማክሰኞ ዕለት አፀደቀ፡፡  የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞች በማሳተፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በዓለም አቀፍም ሆነ አገር አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው፣ ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ የሕፃናትና መብት ማስከበር ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ አዋጁ እንዲፀድቅ የፓርላማው የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ፓርላማው ተቀብሎታል፡፡ የተጠቀሰውን ወንጀል ለመከላከልና የሕፃናትን መብት ለማስከበር ኢትዮጵያ ብቻዋን መንቀሳቀሷ ውጤታማ እንደማያደርጋት፣ ነገር ግን ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ ከሌሎች አገሮች ጋር ተባብሮ በአጋርነት ወንጀሉን መከላከል እንደሚያስችላት ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይም ሕፃናትን በጦርነት ማሳተፍን በሚመለከት የወጣውን የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ተጨማሪ ፕሮቶኮል ፓርላማው በማክሰኞ ውሎው አፅድቆታል፡፡  ም ንጭ፦ http://www.ethiopianreporter.com

በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

Image
አዋሳጥር 21/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት  ከተለያዩ ምንጮች ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ  ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡  የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱም ተገልጿል፡፡  የጽህፈት ቤቱ  የዕቅድ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አክሊሉ እንጀቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ገቢው የተሰበሰበው  ከመደበኛና የማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎትን ጨምሮ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ የታክስ ግብር እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው፡፡  የተሰበሰበው ገቢ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡  በዞኑ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የገቢ ግብር አሟጦ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት  ሌሎች ዝግጅቶችን ጨምሮ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡  ዞኑ ባለፈው የበጀት ዓመትም ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ296 ሚሊዮን  ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ጠቁመው የዞኑን አጠቃላይ ወጪ በሚገኘው ገቢ ለመሸፈን የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡  በዞኑ 15ሺህ 146 ግብር ከፋዮችና 1 ሺህ 535 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች  እንዳሉም ገልፀዋል፡፡  በተያዘው የበጀት ዓመትም 290 ተጨማሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስከአሁን 71 መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡ ምንጭ፦ ኢቲቪ እኣኣ 1/29/2014

Ethiopian Lawmakers Enact Anti-Tobacco Law

Image
The Ethiopian House of Representatives has reportedly ratified the World Health Authority’s Framework Convention on Tobacco Control (FCTC), which places limitations on the sale and use of cigarettes. Besides a ban on smoking in public, the proclamation also includes plans of increasing taxes on cigarette and initiating public campaigns against the hazards of smoking. Campaigns against smoking cigarettes have been gaining ground in sub-Saharan African countries in the past few years. According to experts, given that the market for cigarettes in the western world is well defined, the search for more consumers is quickly spreading to Africa and Asia, where lack of education, poverty and weak legislation makes it relatively easy for tobacco companies to make huge profits. In December 2013, when the draft bill was initially brought before the house, Ethiopian lawmakers expressed disappointment that the country had stalled in ratifying the convention. Like many other African na

Foot Power: York County runners share marathon experience in Ethiopia

Image
By M.C. Besecker To say Clay Shaw is a living legend in the York County racing scene is not a stretch of the imagination at all. Just take a quick look at the facts. Shaw was an inaugural member of the York Road Runners' Club. He directed various races in the area for years, often drawing elite athletes from all along the East Coast. He has run 182 marathons in 22 different countries. Shaw is also a local trendsetter. He has run a marathon in all 50 states, and now several local runners are attempting to duplicate that feat. Not to be outdone, Shaw decided to do it again, embarking on a second tour of our country. He has only two states left to wrap up that second tour: Kansas, which he plans to do in March, and Alaska, later this summer. Shaw might have started this adventure alone, but he has had a partner in crime to keep him company on his many excursions for many years. Wife Karen Mitchell has run 105 marathons, and typically follows Shaw wherever he goes. The mo

የጉቦ ነገር በኢትዮጵያ

Image
መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዢዎች የውጭ ኢንቨስተሮች ጉቦ እንጠየቃለን አሉ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ላይ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች በሙስና ላይ ስላላቸው አመለካከት ለማወቅ በተደረገ ረቂቅ ጥናት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዥዎች እስከ 80 በመቶ ጉቦ እንደሚጠየቁ ተመለከተ፡፡  ይህ አስደንጋጭ ነው ሲሉ ረቂቅ ጥናቱን ያካሄደው ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ አመነ ዲያነ ገልጸዋል፡፡ አቶ አመነ እንደሚሉት፣ ለጥናቱ ከተጠየቁት 350 ኢንቨስተሮች መካከል አንድ መቶ ብር ለሚያወጣ ግዥ 80 በመቶውን ጉቦ የሚጠይቁ አሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ምላሽ የሰጡት ግን ውስን ቁጥር ያላቸው ቢሆንም ሁኔታው አስደንጋጭ ነው ብለዋል፡፡  ባለፈው ሐሙስ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለቤትነት ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ባካሄደው ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ለተካሄደው ጥናት ሐሳባቸውን እንዲገልጹ የተጠየቁት ኢንቨስተሮች ከ42 አገሮች የተወከሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ኢቨስተሮች እንደሚሉት ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ወደ መንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት ጉቦ ይጠየቃሉ፡፡  ከዚህ በተጨማሪም የመረጃ ማረጋገጫ ለማግኘትና ፈቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜ መሻሻል ቢታይበትም፣ አሁንም መስተካከል እንደሚቀረው አመልክተዋል፡፡  በተካሄደው ውይይት ላይ በጥናቱ ጐልተው ከታዩት ውስጥ አነስተኛ ሙስና ገዝፎ ታይቷል፡፡ ነገር ግን ትላልቅ የሙስና ድርጊቶች በሰፊው የሚነገርላቸው በመሆናቸው ሊጤን እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡  በጥናቱ ሕግና መመርያ፣ የቢሮክራሲ ማነቆዎችና ቢዝነስ ለመሥራት ያለው ቅለትና የሙስና ችግሮች አጽንኦት ተሰጥቷቸው ቀርበዋል፡፡  በሦስቱም መስኮች ችግር መኖሩ በረቂቅ ጥ