Posts

የጉቦ ነገር በኢትዮጵያ

Image
መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዢዎች የውጭ ኢንቨስተሮች ጉቦ እንጠየቃለን አሉ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ላይ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች በሙስና ላይ ስላላቸው አመለካከት ለማወቅ በተደረገ ረቂቅ ጥናት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዥዎች እስከ 80 በመቶ ጉቦ እንደሚጠየቁ ተመለከተ፡፡  ይህ አስደንጋጭ ነው ሲሉ ረቂቅ ጥናቱን ያካሄደው ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ አመነ ዲያነ ገልጸዋል፡፡ አቶ አመነ እንደሚሉት፣ ለጥናቱ ከተጠየቁት 350 ኢንቨስተሮች መካከል አንድ መቶ ብር ለሚያወጣ ግዥ 80 በመቶውን ጉቦ የሚጠይቁ አሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ምላሽ የሰጡት ግን ውስን ቁጥር ያላቸው ቢሆንም ሁኔታው አስደንጋጭ ነው ብለዋል፡፡  ባለፈው ሐሙስ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለቤትነት ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ባካሄደው ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ለተካሄደው ጥናት ሐሳባቸውን እንዲገልጹ የተጠየቁት ኢንቨስተሮች ከ42 አገሮች የተወከሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ኢቨስተሮች እንደሚሉት ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ወደ መንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት ጉቦ ይጠየቃሉ፡፡  ከዚህ በተጨማሪም የመረጃ ማረጋገጫ ለማግኘትና ፈቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜ መሻሻል ቢታይበትም፣ አሁንም መስተካከል እንደሚቀረው አመልክተዋል፡፡  በተካሄደው ውይይት ላይ በጥናቱ ጐልተው ከታዩት ውስጥ አነስተኛ ሙስና ገዝፎ ታይቷል፡፡ ነገር ግን ትላልቅ የሙስና ድርጊቶች በሰፊው የሚነገርላቸው በመሆናቸው ሊጤን እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡  በጥናቱ ሕግና መመርያ፣ የቢሮክራሲ ማነቆዎችና ቢዝነስ ለመሥራት ያለው ቅለትና የሙስና ችግሮች አጽንኦት ተሰጥቷቸው ቀርበዋል፡፡  በሦስቱም መስኮች ችግር መኖሩ በረቂቅ ጥ

የጥራት ደረጃ ያጭበረበሩ ሁለት ቡና ላኪዎች በሕግ ሊጠየቁ ነው

Image
- ሌሎች ስድስት ላኪዎች በማስጠንቀቂያ ታልፈዋል -ራሱን የቻለ የመጋዘን አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ሊቋቋም ነው ለውጭ ገበያ የሚቀርብ የቡና ምርት የጥራት ደረጃ በማጭበርበር የወደቀ የጥራት ደረጃ ያለው የቡና ምርት ከአገር ለማስወጣት የሞከሩ ሁለት ቡና ላኪዎች በሕግ እንዲጠቁ መወሰኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ የውጭ ንግድ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ያዕቆብ ያላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት የወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው በቡና ላኪዎቹ ላይ ስለተወሰነው ዕርምጃ ያሳወቁት፡፡ በንግድ ሚኒስቴር ቀጥተኛ ክትትል የሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች የውጭ ንግድ ማስፋፊያ ሥርዓት አፈጻጸምና ውጤታማነት ላይ በ2004 ዓ.ም. በኦዲት የታየ ችግር በመኖሩ፣ ቋሚ ኮሚቴው ችግሩ በምን ዓይነት መንገድ እየተቀረፈ መሆኑን ለማወቅ ነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የጠራው፡፡ በ2004 ዓ.ም. ታዩ ከተባሉት ችግሮች መካከል ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች የጥራት ደረጃ ጉድለት አገሪቱን በእጅጉ እየጐዳ መሆኑን፣ ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚገዙ የግብርና ምርቶች የኪሎ ጉድለት እንደሚታይባቸው፣ ግዥውን የፈጸሙ ላኪዎች የገዙትን የግብርና ምርት በጥራት ደረጃው እንደማያገኙት፣ ወደ ውጭ እንዲላክ የተዘጋጀ ቡና ዋጋ ውጭ አገር ተሽጦ ከሚገኘው ገቢ የሚንር መሆኑ በ2004 ዓ.ም. በዋና ኦዲተር ጄኔራል የተደረገው የክዋኔ ኦዲት ያስረዳል፡፡ ችግሩን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ባለፈው ረቡዕ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ የተጠየቁት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ያዕቆብ፣ አብዛኞቹ ችግሮች መለየት መቻላቸውንና መቀረፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ጥቂት የሚባሉ ነገር ግን ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ቡና ላኪዎች የቡና

በሲዳማ ዞን ለባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

ሐዋሳ ጥር 20/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት ከ24 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የኢንቨስትመንት ካፒታል ላስመዘገቡ 12 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡  በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፋፊያ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ግብርናና ኢንዱስትሪ ይገኙበታል፡፡  ባለሃብቶቹ ለ279 ቋሚና 788 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል ማግኘታቸውን ገልፀው ባለፈው ዓመት በተጀመረ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴም ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡  መምሪያው ለ41 ባለሃብቶች የፍቃድ እድሳትና ተጨማሪ የማስፋፊያ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችን ድጋፍ  በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሂደት ለማመቻቸት ባደረገው ጥረት 320 ፕሮጀክቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡  አዲስ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ከገቡ ባለሃብቶች መካከል አንዳንዶቹ ልማታዊው መንግስት እያደረገላቸው ድጋፍ በርካታ ባለሃብቶች በሃገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረግ ሌላ በድህነት ላይ በሚደረገው ዘመቻ ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡  በሲዳማ ዞን ባለፉት 15 ዓመታት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ770 በላይ ባለሃብቶች በኢንቨሰትመንት መሰክ በመሰማራት ከ56 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠራቸውን አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡ ምንጭ፦ ኢዜኣ 1/28/2014

የኮፒ ፔስት ጉዳይ ወዴት እየወሰደን ይሆን?..............እንዳለ ደበላ ሀዋሳ ኢዜአ

ዘወትር ከሚቀመጡባት የዛፍ ጥላ ስር ዛሬም እንደወትሯቸው ተቀምጠዋል። በተለመደው ሁኔታ ከፊት ለፊታቸው ካለች ሰባራ የእንጨት ባለመደገፊያ ወንበር ላይ የተቀመጡ ደምበኛቸው የመጡበትን ሁኔታ እየገለጹላቸው ነው።  እርጅናና ኑሮ ያጎሳቆለው እጃቸው ቢንቀጠቀጥም እንደወትሮ አስኪሪፕቶ ጨብጦ ከባለጉዳያቸው የሚነገራቸውን ዋና ዋና ሀሳብ በያዟት እንደርሳቸው እድሜ የተጎሳቆለች የምትመስል ማስታወሻ ቢጤ ደብተር ላይ ጫር ጫር ያደርጋሉ።  እንግዳቸው የመጡበትን ጉዳይ አስረድተው እንደጨረሱ ሻምበል ቢተው በተለመደ ሁኔታ በመካከሉ ካርቦን የገባበት የታጠፈ ወረቀት አውጥተው መጻፍ ጀመሩ።  የመጀመሪያውን ጨርሰው ሌላ ሁለተኛ ካርቦን በመካከሉ የገባበት ወረቅት አውጥተው ያለ ምንም የሀሳብ መቆራረጥ በሚንቀጠቀጥ እጃቸው በማስታወሻ ላይ የጫሩትን ሀሳብ መልከት እያደረጉ የቃላት ዝናብ በወረቀቱ ላይ ያዘንቡ ጀመር።  እንደጨረሱ የጻፏቸውን ሁለት ገጽ ወረቀቶች በየተራ አንብበው እንደጨረሱ ለደንበኛቸው አስፈረሙበትና ቴምብር ለጥፈው በክላሰር በማድረግ ሰጧቸው።  ለዚህ አገልግሎታቸው ከደንበኛቸው የክላሰሩንና የቴምብሩን ዋጋ ሳይጨምር የተቀበሉት 20 ብር ብቻ ነው።  ዛሬ ዘመናዊው አለም በፈጠራቸው የጽሁፍ ማሽኖች ሳቢያ የምንጽፋቸው ጽሁፎች ለራሳችንም የማይገቡና ግራ የሚያጋቡ እየሆኑና በኮፒ ፔስት የተሞሉ ጽሁፎች ተበራከተው በመጡበት ወቅት ራፖር ጸሀፊው ሻምበል ያለምንም መመሳሰልና ኮፒ ፔስት የባለጉዳዮቻቸውን ሀሳብ አዳምጠው ያለምንም የሀሳብ መቆራረጥ ለሁሉም በሚገባ መልኩ ያለማቋረጥ ይጽፋሉ።  የደረስንበት የቴክኖሎጂ አለም ስራችንን ቀልጣፋና በአጭር ጊዜ እንድናከናውን የረዳን ቢሆኑም ኢንተርኔትና ፌስ ቡክ አድራጊና ፈጣሪ በመሆን ከአዕምሯችን አፍልቀን እንዳንጽፍ እን

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ብሄራዊ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነውን መድረክን "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia" ልቀላቀል መሆኑ ተሰማ

Image
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በጠራው ጉባኤ በድርጅቱ የወደፊት የትግል ኣካሄድ ላይ በመወያየት ወሳኔዎች ኣሳልፏል። ቅዳሜ ቀን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ እስከኣሁን ድረስ የተከተለውን የትግል ስልት የገመገመ ሲሆን፤ ይከተለው የነበረው የተናጠል የትግል ስልት ፖለቲካዊ ግቦቹን ለማሳካት እንዳላስቻለው ኣመልክቷል። በመሆኑም በችግሮቹ መፍትሄ ላይ በስፋት በመምከር፤ ለተሳካ የፖለቲካ ትግል ከሌሎች መሰል ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመታገል ወስኗል። በውሳኔው መሰረት በኣሁኑ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia - Medrek '' መድረክን '' በመምረጥ መድረክን በመቀላቀል በጋር ለመስራት መወሰኑን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል። ክቡራን ኣንባቢያ በሲኣን ውሳኔ ላይ ያላችሁን ኣስተያየት በምከተለው ኣድራሻ ላኩልን: nomnanoto@gmail.com ጥቂት ስለ መድረክ፦ Medrek  (officially the "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia") is an  Ethiopian  opposition political coalition founded in 2008 which contested the  Ethiopian general election, 2010 . In thatelection, Medrek won a single seat in the  Council of People's Representatives , representing an electoral district in  Addis Ababa . [1]  This was allegedly d