ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ራሳቸውን ከፖለቲካ አገለሉ
‹‹የሕዝብ መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የአንድነትን አቋም ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት ያስቸግራል›› m አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር የነበሩትና ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ከጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት የወሰኑት አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስላልተመቻቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ምላሽ ባለማግኘታቸው መሆኑን በተለይ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት፣ መድረክ ግንባር ከመሆኑ አስቀድሞ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ሁሉም ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ ከተወያዩባቸው በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ መስማማታቸውንም ለመድረክ በመግለጽ መድረክ ወደ ግንባር መሸጋገሩን አስታውሰዋል፡፡ በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. በአንድነት ፓርቲና በእሳቸው የአመለካከት፣ የአቋምና የአቅጣጫ ልዩነት መፈጠሩን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ግንባር የተቀየረው በጠቅላላ ጉባዔውና በብሔራዊ ምክር ቤቱ እምነትና ውሳኔ ሳይሆን በአመራሮች መሆኑን በመጥቀስ፣ እንደማይስማማ በዚያን ወቅት ባደረገው ግምግማ ላይ በመግለጹ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ መድረክ ወደ ግንባር ከመቀየሩ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተውና ተመካክረው በሕገ መንግሥት ጉዳይ፣ በቤት ጥያቄና በሌሎችም በተነሱ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕገ መንግሥቱ አ