የሃዋሳ ከተማ በኢትዮጵያ የከተሞች ውድድር በተደጋጋም ኣሸናፊ መሆን የሲዳማውያ የማስተዳደር ብቃት ማረጋገጫ ነው፤ ከተማዋ ኣየር ማረፊያ ልገነባላት ነው
የሲዳማ መዲና የሆነችው ሃዋሳ ከተማ ላለፉት 19 ኣመታት የከተማዋ ባለበት በሆኑት የሲዳማ ተወላጆች መተዳደር ከጀመረች ወዲህ በመጤዎች ለግማሽ ምዕተኣመት ሲትተዳደር ካሳየችው እድገት በላይ በማስመዝገብ በኣሁኑ ጊዜ በኣገሪቱ ከምገኙ ግንባር ቀደም የክልል ከተሞች ኣንዷ ልትሆን በቅታለች። ብሎም ከተማዋ ኣገሪቱ በማስመዛገብ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ እድገት ተጨባጭ ማሳያ ሆናለች። ሃዋሳ በተለይ ባለፉት 10 ኣመታት ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲትሆን በማለም ትምህርት እና ጤናን ጨምሮ በሌሎች መሰረታዊ ኣገልግሎት ዘርፎች፤ በመንገድ፤በኃይል እና ውሃን ጨምሮ በሌሎች ኢንፍራስትራክቼርን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ ስራዎች ከተሰሩባቸው የኣገሪቷ ከተሞች ኣንዷ ናት። በመልካም ኣስተዳደር ላይ የምታዩትን ኣንዳንድ ችግሮችን በመቅረፍ ስራዎች በከተማዋ ኣስተዳደር በመስራት ላይ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ መልካም ውጤት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። እንግዲህ የሃዋሳ ከተማ በየኣመቱ በምካሄደው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ውድድር ላይ ለነዋሪዎቿ ኑሮ ምቹነት በተለያዩ ዘርፎች ባካሄደቻቸው መልካም ስራዎች በምርጥ ከተማነት በመመረጥ በተደጋጋም ኣሸናፊ መሆኗ ከተማዋን የሚያስተዳድሩት ሲዳማውያ ኣይደለም ከተማ እና ዞንን ቀርቶ ክልልን በብቃት ማስተዳደር እንደምችሉ ያስመሰከሩበት ነው። የሃዋሳ ከተማ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የከተማዋ ኣስተዳደር ለያዘው እቅድ መሳካት ኣስተዋጽኦ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል የኣውሮፕላን ማረፊያ መኖር ወሳኝ ቢሆንም ከተማዋ ያለ ኣውሮፕላን ማረፊ ቆይታለች። ለሃዋሳ ከተማ በኣየር ማረፊያነት የሚያገለግለው ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ፊትለፊት ያለ ሜዳ ሲሆን፤ ይህ ሜዳም ሂልኮፕቴር እና ትናንሽ ኣውሮፕላኖች ለማሳረፊያነት ያለፈ ኣገልግሎች