የሃዋሳ ከተማ የጸጥታ ችግር ተቀርፎ ይሁን?
በሃዋሳ ፀጥታን የማስከበር ሥራ ለነዋሪው እፎይታ አስገኝቷል ብዙዎቹ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በአካባ ቢያቸው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለብዙ ጊዜ ተቸግረዋል። በገዛ አካባቢያቸው በሰላም መውጣትና መግባት ያለመቻላቸውን ሲያስታውሱ ይማረራ። የፀጥታው ችግር የተፈጠረው ደግሞ በገዛ ወጣቶቻቸው መሆኑ የምሬታቸውን መጠን ከፍ ያደርገዋል። የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መዲና በሆነችው በሃዋሳ መሀል ክፍለ ከተማ የለኩ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መሠረት ወንድሙ በቀበሌያቸውም ሆነ በክፍለ ከተማቸው ከእዚህ ቀደም ብዙ ፈተና ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። ትንሽ መሸት ካለ ሰዎች እንደ ልብ ወዲያና ወዲህ መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ያሰቡትን ማሳካት አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱን ያመለክታሉ። « ጨለማን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሰውን ሰው ሰላምና ፀጥታ ማደፍረስ በአካባቢያችን የተለመደ ሆኖ ቆይቷል። ማንነታቸውንም ለመለየት ደግሞ ሰዎች ፍራቻና ስጋት ስለሚያድርባቸው በየጊዜው ወንጀል ይከሰት ነበር። ችግር የፈጠረውን ግለሰብ አሳልፎ ለሕግ የማቅረብ ድፍረቱም አልነበረም » ይላሉ ወይዘሮዋ። ዛሬ ግን ይህ አስቻጋሪ ወቅት አልፏል። ለእዚህ ምክንያቱ ደግሞ የሰላምና የፀጥታ ችግር የሆነውን ጉዳይ ሕዝቡ በጋራ ስለመከረበት ነው። በፀጥታው መደፈር የታከተው ሕዝብ እርስ በእርስ በመወያየቱም ወደ መፍትሔ ሊመጣ ችሏል። መፍትሔ ሆኖ ለውጥ አምጥቷል ከሚባሉት መካከል አንዱ የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ መቋቋም ነው በማለት ይገልጻሉ። አሁን ሲያሰጋቸው የነበረው ችግር ሙሉ ለሙሉ መወገዱን የጠቀሱት ወይዘሮ መሠረት በሰላም ወጥተው መግባታቸው ለሥራቸውም ሆነ ለከተማዋ ልማት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን ይናገራሉ። የአካባቢውም ነዋሪ የመንገድ