‹‹የፖለቲካ ባህሉ መሠረት እንዲይዝ ብዙ ትግል ይጠይቃል››
አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል የነበሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከሃያ ዘጠኙ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ... ኮሚሽን አባላት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በዲግሪ የተመረቁት አምባሳደር ታዬ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ነበር ሥራ የጀመሩት፡፡ ይሁንና ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ በቆየው አገልግሎታቸው በዲፕሎማትነት፣ በቆንስላ ጄነራልነት፣ በአምባሳደርነትና በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ውስጥ አገልግለዋል፡፡ በተለያዩ አገሮች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ የሠሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ስዊዲንና አሜሪካ ይገኙበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ሰለሞን ጎሹ የዛሬ 19 ዓመት ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. ፀድቆ በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የማርቀቅ ሒደትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አምባሳደር ታዬን አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- እርስዎ አባል የነበሩበት የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አሁን በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በማርቀቁ ሒደት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ የሽግግሩ ዘመን ቻርተር የሽግግር መንግሥቱ ሕገ መንግሥት በማርቀቅ እንደሚያበቃ ይገልጻል፡፡ አጠቃላይ ሒደቱ ምን ይመስል ነበር? አወቃቀሩስ ምን ይመስል ነበር? በማርቀቅ ሒደቱ ተጨማሪ ሚና ከነበራቸው ሌሎች ተቋማት ጋርስ የነበራችሁ ግንኙነት እንዴት ነበር? አምባሳደር ታዬ ፡- የሽግግር መንግሥቱ ዋነኛ ተግባር ሕገ መንግሥት አዘጋጅቶ ሥልጣኑን በሕዝብ ለተመረጠ አካል