Posts

What happen to Yirgalem Restaurant in Madison

Image
Read more@ http://www.ethiopianrestaurant.com/wisconsin/yirgalem.html

Hawassa University Marks Farmers’ Field Day at Boricha and Dale Woredas

Image
 To see more Photos@ http://www.hu.edu.et/hu/index.php/84-hawassa-university/events/news/378-hawassa-university-marks-farmers-field-day-at-two-of-its-technology-villages

የስደት ውርደት በዛ! ሥራም ይፈጠር ኢትዮጵያዊነትም ይከበር

Image
በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውና እየተስተጋባ ያለው አሰቃቂ ግድያና ድብደባ ይዘገንናል፣ ይሰቀጥጣል፣ ያቅለሸልሻል፡፡ አረመኔያዊ ነው፡፡  የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የራሱን ሕግ ማስከበር እንዳለበት እናምናለን፡፡ በሕገወጥ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የገቡትን ሰዎች ወደ አገራቸው ቢመልስ ወይም ቢያባርር ተቃውሞ የለንም፡፡ ጥያቄያችንና ተቃውሞአችን ግን በሕገወጥ መንገድ የገቡትን ኢትዮጵያውያን ለምን መለስካቸው?ለምን አባረርካቸው?የሚል አይደለም፡፡ ሕገወጦችን መቆጣጠርና ሕግን ማስከበር የማንም አገር መብትና ኃላፊነት ነውና፡፡ ግን! ነገር ግን! በሕገወጥ መንገድ የገቡትን ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ አገራቸው ይመልሳል ወይም ይቀጣል እንጂ፣ ግድያና ማሰቃየት ማካሄድ የለበትም፣ አልነበረበትም፡፡  እኛም እንደምንከታተለው የዓለም መገናኛ ብዙኃንም እያስተጋቡት እንዳለው፣ በመጀመሪያ ከኢትዮጵያ የሄዱት የቤት ሠራተኞች እንደ ባርያ እንጂ እንደ ነፃ ሰው አይታዩም፡፡ እንደ እንስሳና እንደ ባርያ ነው የሚቆጠሩት፡፡ በሕጋዊ መንገድ የገቡትም ጭምር፡፡  ከዚያም አልፎ በየቤቱ ፖሊስ እየገባ ሕገወጥ ናችሁ እያለ ሲገድልና አስከሬን በየጎዳናው ሲወረውር በግልጽ በሚስቀጥጥ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ የሳዑዲ መንግሥት የራሱን ሕግ የማስከበር መብት እንዳለው ሁሉ፣ ማክበር ያለበትና የሚገደድባቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎች እንዳሉም ሊገነዘብና ሊተገብር ይገባዋል፡፡  በተለይም በዘፈቀደ አንዳንድ የሳዑዲ ዓረቢያ ተወላጆች የሚፈጽሙት ግፍ አልበቃ ብሎ፣ የመንግሥት የፀጥታና የፖሊስ ኃይል ቤት ለቤት እየገባ ግፍና ወንጀል በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ሲፈጽም፣ በማያወላዳ መንገድ ዓለም አቀፍ ሕግን መጣስ ነው፡፡ ሕግ መጣሱና ወንጀ

Indigenous crops like ''Wesse'' feeding the world

Image
Imperial, California - Potatoes may seem fairly humble, but there are more than 4,500 species of potato in the world. Likewise, there are at least 1,000 pepper plant varieties, 7,500 tomato species, and 7,500 known apple varieties worldwide. However, the incredible variety of the planet’s plant life is disappearing. The U.N. Food and Agriculture Organization (FAO) reports that approximately 75 percent of the Earth’s plant genetic resources are now extinct. Another third of plant biodiversity is expected to disappear by 2050. This is no small problem--humans eat biological diversity. Unfortunately, most investment in agriculture is for crops such as wheat, rice, and maize, rather than more nutritious foods--and this focus has had devastating consequences. Global obesity rates have doubled over the last 30 years, increasing the risk of diet-related illnesses including diabetes, hypertension, and heart disease in industrialized and developing countries alike. But many indigenous cro

የሸበዲኖና የአለታ ወንዶ አርሶ አደሮች የቡና ዋጋ መቀነስ አሳስቧቸዋል፤የአንድ ኪሎ እሽት ቡና ዋጋ ከድንች ዋጋ ጋር መቀራራቡ አርሶ አደሮቹን አሳስቧቸዋል

Image
ቡና ልብሳቸው፣ ምግባቸው፣ ጌጣቸው፣ መዝናኛቸው እንዲሁም መድመቂያቸው እንደሆነ የሲዳማ ዞን አርሶ አደሮች ያለአንዳች ማመንታት ይናገራሉ። ቡና ሸጠው ቤታቸውን ይገነባሉ፣ ቡና ሸጠው ልጆቻቸውን ያስተምራሉ እንዲሁም ቡና ሸጠው ሀብት ንብረት ይቋጥራሉ። ቡና አፍልተው የሩቁንም ሆነ የቅርቡን ወዳጃቸውን እንዲሁም ዘመድ አዝማድን ያስተናግዱበታል። ታዲያ በዞኑ ካሉት አርሶ አደሮች መካከል ቡና በማሳው አልያም ደግሞ በጓሮው ያልተከለ የለም ለማለት ያስደፍራል። ከማጀታቸውም ቢፈለግ የታጠበ አሊያም ደግሞ እሸት ቡና አይታጣም - አሁን ቡና የሚለቀምበት ወቅት ነውና። በአገር አቀፍ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ ስም ያለውን ቡና የሚያመርቱት የእዚህ ዞን ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ቀደም ባሉት ጊዜያት ምንም እንኳ ቡና የማምረቱን ሂደት በራሳቸው የአመራረት ስልት ማምረት ባያቋርጡም የምርቱ ተጠቃሚ አልነበሩም። ይልቁንም ይላሉ የዞኑ አርሶ አደሮች  « እኛ በለፋንበትና በደከምንበት ነጋዴውና በመሀል ያለው ደላላ ምርቱ ላይ አያዋጣኝም ያዋጣኛል በሚል ድርድር ኪሳቸውን ሲሞሉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር »  ይላሉ። ምንም እንኳ በዞኑ ያሉ አንዳንድ መሠረታዊ ማህበራት የተቋቋሙት በ 1968 ዎቹ ዓመተ ምህረት አካባቢ ቢሆንም አርሶ አደሩ የአሁኑን ያህል በወቅቱ ከማህበራቱ አለመጠቀማቸውንም ሳይገልጹ አላለፉም። ከቡና ምርታቸውም ሆነ በማኅበር በመደራ ጀታቸው አሁን አሁን ይበልጥ ተጠቃሚ እያደረ ጋቸው መምጣቱን የሚጠቅሱት አርሶ አደሮቹ በተለይ የዓለም የቡና ገበያ የተረጋጋ ነው ተብሎ ከዛሬ አራት ዓመት በፊት ሲሸጥ የነበረበት ዋጋ ለድካማቸው መልካም የሆነ ምላሽ የሚሰጥ እንደነበር ያመለክታሉ። አምናና አቻምና ግን  « በድካማችን ልክ ያለማግኘታ ችንን እንቆቅልሽን ማ