በመልካም አስተዳደር ከ52 የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያ 33ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
ከ11 የምስራቅ አፍሪካ አገራት ደግሞ በ8ኛ ላይ ተቀምጣለች መልካም አስተዳደር ከ100% ሞሪሺየስ - 80 ቦትስዋና - 78 ኬፕቨርዴ - 77 ሲሸልስ - 78 ደቡብ አፍሪካ - 71 ሶማሊያ - 8 የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የ2013 የመልካም አስተዳደር ውጤታማነት ደረጃን “Ibrahim Index of African Governance (IIAG)” ይፋ ያደረገው ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር፡፡ በመልካም አስተዳደር ምርጥ ተብላ ከአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ የተቀመጠችው ሞሪሺየስ ስትሆን የመጨረሻዋ አገር ሶማሊያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ከ52 የአፍሪካ አገራት 33ኛ ደረጃ ተሰጥቷታል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን የመልካም አስተዳደር ሁኔታ በአራት መስፈርቶች የገመገመው የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፤ ባለፉት 10 ዓመታት በሰው ሃብት ልማት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ገልፆ፤ በዋናነት በጤና እና በትምህርት መስኮች ለውጥ መመዝገቡን አመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከ52 የአፍሪካ አገራት 33ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከ100 ነጥብ 47.6 በማግኘት ሲሆን የአፍሪካ አማካይ ነጥብ 51.6 ነው ይላል ፋውንዴሽኑ፡፡ ኢትዮጵያ ከ11 የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ተወዳድራም በ8ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠች የጠቆመው የፋውንዴሽኑ መረጃ፤ በዚህ የአፍሪካ ቀጠናም ኢትዮጵያ የሚጠበቀውን የ47.9 አማካይ ነጥብ አለማግኘቷን አመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት በመልካም አስተዳደር ያላትን ደረጃ ያሻሻለችው በ5.1 ብቻ ነው ይላል፤ መረጃው፡፡ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን “ኢብራሂም ኢንዴክስ ኦፍ አፍሪካን ጋቨርናንስ” ሪፖርት፤ የአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ በመልካም አስተዳደር መሻሻል እንዳሳዩ ጠቁሟል፡፡ አገራቱ የተመዘኑት የመልካም አስተዳደር መገለጫ ናቸው ተብለው በሚታ