ሃዋሳ፦የመናፈሻ ፓርክ ብርቅ የሆነባት ከተማ
ሃዋሳ ከተማ የሲዳማ መናገሻ በኣለማችን ላይ በርካታ ዘመናዊ ከተሞች በተለይ በኣሁኑ ጊዜ ከኣለም የኣየር ሙቀት ጋር ተያይዞ ብሎም ለከተሞቹ ውበት እና ለከተሞቹ ነዋሪዎች ምቾት ሲባል በርካታ የመናፈሻ ፓርኮችን እየገነቡ እና ለኣገልግሎት እያበቁ ይገኛሉ። መናፈሻ ፓርኮች በከተሞች መኖራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች በእረፊት ጊዚያቸው ንጽህ ኣየር እየተነፈሱ ኣልያም በለምለም ዞፎች መካከል እየተንሸራሸሩ ጊዚያቸውን እንድያሳልፉ ያስችላቸዋል። ለኣብነት ያህል ኣብዛኛውቹ የደቡብ ኣሜሪካ ኣገራት ከተሞች ማለትም ከትናንሾቹ እንስቶ እስከ ሜክስኮ ሲቲ እና የብራዚሏን ሳኦፖሎን የመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች እያንዳንዱ የከተሞቹ መንደረ በፕላዛ ወይም በግሪንኤሪያ የተሞሉ ናቸው። እነዚህ ፓርኮች በከተሞቹ ነዋሪዎች ተሞልተው ይውላሉ። ፓርኮቹ የተለያዩ የስፖርት ማዘወተሪያ ማዕከላትን የያዙ በመሆናቸው በርካታ ወጣቶች ጊዚያቸውን ኣልባለ ቦታ ከማሳለፍ በተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች ላይ እንዲያሳልፉ ኣስችሏቸዋል። በደቡብ ኣሜሪካ የከተሞች ውበት የምለካውም በያዙት ፓርኮች እና በፓርኮቹ ውበት ነው። በርግጥ የከተሞቹ ውበት እና ንጽህና የነዋሪዎቹን ስልጣነ ያሳያል። የሰሜን ኣሜሪካ ወይም የኣውሮፓ ከተሞችንም ሲንመለከት በውብ ፓርኮች የተሞሉ ናቸው። የየከተሞቹ ኣስተዳደር ለፖርኮች ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ስጥተው ይሰራል። ነዋሪዎችን ከየከተሞቹ ኣስተዳደር በላይ ለፓርኮቹ ውብ እና ንጽህ መሆን የበኩላቸውን ይወጣሉ። ከኣውሮፓ እና ከደቡብ ኣሜሪካ ከተሞች ፊታችንን ወደእኛዋ ከተማ ስንመልስ ሌላ ታሪክ ነው የምናየው። የሲዳማዋ ዋና ከተማ ሃዋሳ ከሊባኖስ ተነስቶ እስከ ሞዛሚብክ ለምዘንቀው ታላቁ ስምጥ ሸለቆ እምብርት ላይ የምትገኝ ከመሆኗ የተነሳ ሞቃት ኣየር ኣመቱን ሙሉ