የሲዳማ ቡና ኣምራቾች የተሳተፉበት በቡና ጥራት ላይ የምመክር ጉባኤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ
ሲዳም ቡና በወኢኔ በጉባኤው ላይ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ እና የደቡብ ክልል ኣዲሱ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ ዳልኬን ጨምሮ ጉዳዩ የምመለከታቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል። ከሃዋሳ ያገኘነው መረጃ እንደምያሳየው ፤ኣገሪቱ ዘንድሮ ከ 277 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጪ ገበያ በማቅረብ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዳ ለች ለዚህም ደቡብ ክልል ጨምሮ በየክክሉ የሚመረተው ቡና ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ በብዛት መቅረብ ኣለበት ተብሏል ። እንደ ኢዜኣ ዘጋባ ፤ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ከሲዳማ እና ከሌሎች በደቡብ ክልል ቡና አምራች ዞኖችና ልዩ ወረዳ አመራሮች ጋር ትናንት በሀዋሳ ባደረጉት ውይይት ላይ እንዳሉት ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ ዘንድሮ ለውጪ ገበያ ከሚያቀርባቸው የኤክስፖርት ሰብሎች ከ 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል ። ኣክለውም ከግብርና ምርት፣ ከማኑፋክቸሪንግና ከማዕድን ዘርፎች ለመሰብሰብ ካቀደው የውጪ ምንዛሪ ውስጥ 90 በመቶ ከግብርና ምርቶች የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ ቡና ከፍተኛውን ድርሻ እንደምይዝ ኣብራሪተዋል ። በ 2004 ዓ . ም 169 ሺህ ቶን የታጠበና ደረቅ ቡና ለውጪ ገበያ በመላክ 832 ሚሊዮን ዶላር በ 2005 ዓ . ም ከቀዳሚው ዓመት በ 30 ቶን ብልጫ ያለው ቡና የቀረበ ቢሆንም በቡና ዋጋ መቀነስ ምክንያት 740 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ ገልፀዋል፡፡ ዘንድሮ ቡናን በብዛት በመላክ ገቢውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል። በደቡብ ክልል ከፍተኛ በቡና የተሸፈነ ማሳ ያለ ቢሆንም በአቅርቦት ማነስና በጥራት መጓደል ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ገቢ ማግኘት ሳይቻል እንደቆየና ይህን የአቅርቦት ውስንነትና ጥራት መጓደል በማስቀ