Posts

በሀዋሳና በሌሎች የኣገሪቱ ከተሞች የኢንዱስትሪ ዞኖችን ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ለኢንዱስትሪ ዞንነት በተመረጡት አራት ከተሞች ላይ የኢንዱስትሪ መንደር ለማቋቋም የሚያስችለው ጥናት እየተገባደደ ነው ተባለ። የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ አህመድ አብተው እንዳሉት ፥   በአዲስ አበባ ድሬድዋ ፣ ሀዋሳና ኮምቦልቻ ሊገነቡ የታቀዱትን የኢንዱስትሪ ዞኖች  ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው። ከጥናቱ በተጓዳኝ መንደሩን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ የማፈላለግ ሰራም እየተካሄደ ነው። በዚህ መሰረት ከአንድ የእስራኤል ድርጅት ጋር በኮምቦልቻ የሚገነባው የኢንዱስትሪ መንደር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ነው ሚነስትሩ የተናገሩት። በተመሳሳይ በአዲስ አባባ ለሚ ሳይት ከተገነባው በተጨማሪ ሌላ የኢንዱስትሪ መንደር ለመገንባትም ከአለም ባንክ ጋር ንግግር ተጀምሯል። በድሬድዋና በሃዋሳ ለሚገነቡት የኢንዱሰትሪ መንደሮችን ከመንግስት ጋር በመተባባር የመገንባት ፍላጎት  ያላቸው ድርጅቶችም የአዋጭነት ጥናት እያደረጉ ነው ተብሏል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5555:2013-09-28-06-15-48&catid=102:slide

“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” - ተቃዋሚዎች

 “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ። ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!)

ጸረ _ረሃብ ተክል፦ የሲዳማ ዌሴ

Image
Africa faces over the next decade an ever-increasing need to achieve sustainability in agricultural production. In the Horn of Africa one of the primary obstacles to sustainability has been the threat of famine. Yet, as this important booklet shows, there are parts of Ethiopia that survived famine during the 1980s because of the utilization of enset as part of the subsistence system. Also known as the false banana, enset is very likely the most unstudied domesticated crop in Africa. It helps to feed approximately ten million people in Ethiopia and Eritrea (in restricted pockets). Given that it figures so importantly in the diet of contemporary Ethiopians and that it has acted as a famine buffer, why has it been so neglected? The answers are complex. They are partly related to cultural perceptions, politics, and history. This short monograph unwraps much  of the mystery surrounding enset. It explores its history, noting that enset was once much more widespread in Ethiopia. It also

በጤና ተቋማት የሚወልዱ የሲዳማ እናቶች ቁጥር መጨመሩ እየተነገረ ነው

Image
Recién nacido en Aroressa (©F. Schwieker-Miyandazi). አዋሳ መስከረም 16/2006 በሲዳማ ዞን በአንድ ለአምስት አደረጃጀትና በጤና ልማት ሰራዊት የተቀናጀ ጥረት በተከናወኑ ስራዎች በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ አበበ በካዬ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረግ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አበረታታች ነው፡፡ በዞኑ ሁሉም ወረዳ በአንድ አምስት አደረጃጀት፣ በጤና ልማት ሰራዊትና በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት ህብረተሰቡን በማስተባበር የተከናወኑ ስራዎች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ40 ሺህ በላይ እናቶች በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ተጠቀሚ መሆን በመቻላቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ10 ሺህ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡ መምሪያው የወሊድ አገልግሎቱን በሁሉም ጤና ተቋማት በነፃ እንዲሰጥ በማድረጉ ወደ ጤና ተቋም ሄደው የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድና የድህረ ወሊድ እንዲያገኙ ድጋፍ መደረጉ ለቁጥሩ መጨመር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ የወሊድ አገልግሎት ካገኙት እናቶች መካከል 11 ሺህ በአዋላጅነት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ሲሆን ቀሪዎቹ በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በየቀበሌው የተመደቡ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ሁሉም እናቶች ከጤና ተቋም ውጭ እንዳይወሊዱ የሚያደርጉት ሁሉ አቀፍ ጥረት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ባለፉት ሶስት ዓመታት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቷል፡፡ የቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎቱን በማጠናከር ከወሊድ ጋር በ

"On this mission I will be teaching, counseling and spreading the Gospel of Jesus the Christ to the people who live in Hawassa," Ingraham explained. "

Image
  Dunnigan pastor hopes to weld ties with Ethopia A Dunnigan pastor is raising money - and prayers - to establish a church in Ethiopia. Pastor Lashanna Ingraham, 27, of Dunnigan's Body of Jesus the Christ Church has been invited on a two-year mission trip to Hawassa, Ethiopia by Pastor Bereket Asnake of Hawassa's Siloam Reformation Messenger's Church. "On this mission I will be teaching, counseling and spreading the Gospel of Jesus the Christ to the people who live in Hawassa," Ingraham explained. "(I will be) visiting their local churches and college, where approximately 3,000 locals and students gather on the college grounds every Friday for the opportunity to hear the word of God." Ingraham needs to raise $10,000 for the overseas trip, which is not the first exotic location to which Dunnigan's Body of Jesus the Christ's church has spread. Dunnigan's leader and founder, Pastor Herman Brown, works to train mini