የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ
የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡ በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡ በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡ በሥነ