Posts

Opposition: Ethiopia police block rally, beat some

Opposition: Ethiopia police block rally, beat some The Associated Press Monday, Sept. 2, 2013 | 12:07 a.m. An opposition leader in Ethiopia says police have prevented his group from staging a rally to demand the release of jailed activists. Yilkal Getnet, who heads the opposition Blue party, said Sunday that police raided their headquarters in the capital, Addis Ababa, on Saturday night and beat up some party members. He said police also seized banners and equipment that would have been used during a street protest on Sunday. Yilkal says the rally was meant to highlight the continued detention of some journalists and Muslim activists. Ethiopia has charged at least 28 Muslims activists with terrorism. But those activists say they have been unfairly targeted by the government, which they accuse of harassment. A spokesman for Ethiopian police was not immediately available for comment. http://www.lasvegassun.com/news/2013/sep/02/af-ethiopia-protest/

በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየመከሩ ነው

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 27/2005 በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየመከሩ ነው። ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የምክከር መድረክ የከፈቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሐኖም አንዳሉት በዲፕሎማሲ ሰራዊት ግንባታ፣በቢዝነስ ዲፕሎማሲ፣በንግድ፣በቴክኖሎጂ ሽግግር፣በኢንቨስመንት፣ብድርና እርዳታ በማፈላለግ፣በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን በማንቀሳቀስ፣ በባህልና ቱሪዝም ረገድ አምባሳደሮቹ ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በስፋት ይገመግማሉ። ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ሰላም እኳያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለው ግንኙነት በተለይም ከሁለቱ ሱዳኖች ከግብጽና ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ ጥልቅ ውይይት ይካሄዳል ብለዋል። በስራ አፈጻጸማቸው መልካም ተመክሮ ያላቸው ኤምባሲዎች ልምዳቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት ልዩ መድረክም ተመቻችቷል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ቋሚ መልእክተኛ ዶክተር ተቀዳ አለሙ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ጥቅም ከማራመድ ባሻገር የአካባቢውን አገራት እና የአፍሪካን ጥቅም በሚገባ የምታስከብር አገር ስለመሆኗ ጠንካራ አመኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ሊመቀንበር በመሆኗ የአህጉሪቱን ጥቅም ለማስከበር በመርህ ላይ ተመስርታ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገች በመሆኗ በመንግስታቱ ድርጅትና በአፍሪካ አገራት ዘንድ ያላት ተቀባይነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጥቅምና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመመሰረት የበርካታ አገራት ፍላጎት መሆኑንም ጠቁመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍ

ፉራ የልማት ምርምር ማዕከል ከየት ደረሰ? በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው? መረጃ ያላችሁ ሰዎች ኣጋሩን

Image
New

Fichchee – Sidama People’s New year and Tradition – Best Documentary

A documentary video about the Sidama New Year, Fichchee Chembelala : Celebration, Culture and Tradition in Sidamo, Ethiopia.  Fichchee – Sidama People’s New year and Tradition – Documentaryition-documentary/

የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አይተገበሩም ተባለ

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 24 ፣ 2005 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንሰ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የሚሰራውን ሰራ ለማሳካት በመስኩ የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አንዲተገበሩ አሳሰበ። በፋይናንስ ግልጸኝነት ዙሪያ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዳራሽ ዛሬ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደስ እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ ከፋይናንስ አሰራሯ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ያደረገቻቸው ህጎችና መመሪያዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን እና በዚህ ረገድ እየተከናወነ ያለው ስራ በየጊዜው ለውጥ እየታየበት መሆኑን አንስተዋል። ይሁንና ህጎች በአግባቡ አለመተግበርም እየታዩ ያሉ ችግሮች በመሆናቸው የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ በመተግበር ረገድ የሚመለከታቸው ሁሉ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ነው ያሳሰቡት። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት ቡድን መሪ አቶ አለባቸው በላይነህ በበኩላቸው ፥ የፋይናነስ ግልጸኝነትን ለማስፈን በሚሰራው ስራ ሰፊ የግንዛቤ ማስፊያ ስራዎች እየተከናወነ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋማት ችግሮቹ ሳይፈጠሩ በፊት ማከናወን የሚገባቸውን ሁሉ በአግባቡ መወጣት አለባቸው ነው ያሉት ህብረተሰቡም ከሚበጀቱ ፋይናንሶች ጋር በተያያዘ በየጊዜው ግንዛቤው እያደገ መምጣቱን በማንሳት ። የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም የተለያዩ ክልሎች የሚመለከታቸው አካላት የስራ ሀላፊዎች  በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተዋል።