Posts

ፊቼ እና ጫምባላላ - የሲዳማ ዓመት ዋዜማና መባቻ

Image
የአንድ ማኅበረሰብ መገለጫና መለያ ከሆኑት እሴቶች አንዱና ዋነኛው ባህል እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ የአንድ ማኅበረሰብ የኑሮ ዘይቤ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መርሕ እምነትና አስተሳሰብ የጥበብ፣ የአስተዳደር፣ የአለባበስና አመጋገብ ሥርዓት፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችና መገልገያዎች የባህል መገለጫዎች ሲሆኑ በዋናነት በሁለት የሚከፈሉት ቁሳዊና መንፈሳዊ ተብለው ነው፡፡ ቁሳዊ ባህል ታሪካዊ ቅርሶች በጽሑፍ የተቀመጡ ሕትመቶችና ሰነዶች ሕንፃዎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች የምርትና አገልግሎት መሳሪያዎችንና ሌሎች ተያያዥ ውጤቶችን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊ ባህል በሌላ በኩል የሃይማት ( እምነት ) ፣ ፍልስፍና፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች ( ክብረ በዓላት ) እና አመለካከቶችን ያካትታል፡፡   የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፈቼና አዲሱ ዓመት ክብረ በዓል መንፈሳዊ ( ኢንታንጀብል ) ባህል ከሆኑት አንዱ ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫ እንደሆኑ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዓመታዊ መጽሔት ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሲዳማ የራሱ የሆኑ የቀን አቆጣጠር ያለው ሲሆን የአሮጌው ዓመት ማለቂያ እና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ   ትክክለኛ ዕለት የብሔሩ   ሊቃውንት ( አያንቶ ) ተወስኖ ይታወጃል፡፡ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በዓለም መንፈሳዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ቅድመ ምዝገባ የመጀመሪያ ዙር መረጃ የማሰበሰ