የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ለማየት ያጋጠመው ችግር እየተቃለለ ነው
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ 2005 ዓም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት 11/12/2005 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ይፋ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ ተፈታኞቹ ውጤታቸውን በተቋሙ ድረ ገፅ በ www.nae.gov.et እና በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አጭር መልዕክት በመላከ ማወቅ እንደሚችሉ ገልፆ ነበር፡፡ ይሁንና የተወሰኑ ተጠቃሚዎች መረጃውን ያገኙ ቢሆንም በርካታ ተጠቃሚዎች ግን ወደ ኢሬቴድ በመደወል የተባለውን መረጃ ለማግኘት እንደተቸገሩ ነግረውናል፡፡ በጉዳይ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ችግሩ ሁሉንም ጠያቂዎች ባንድ ላይ ማስተናገድ ባለመቻሉ የተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡ ሃላፊው እንዳሉት አሁን በአጭር የስልክ መልዕክት መረጃውን የሚያደርሰው የመረጃ ቋት በአንድ ደቂቃ ማስተናገድ የሚችለው ከ5ሺ እስከ 7ሺ ጥያቄዎችን ነው፡፡ ይሁንና ወደ መረጃ ቋቱ ከ 20ሺ በላይ ጥያቄዎች በአንድ ደቂቃ ዉስጥ ይደርሳሉ፡፡ ለአንድ ተማሪ ዉጤት ከ20 እስከ 30 ሰዎች ያክል ጥያቄ ማቅረባቸው ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ብለዋል ሃላፊው፡፡ ይህም በማዕከሉ ላይ መጨናነቅ በመፍጠሩ በርካታ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን እንዳላገኙ ተረድተናል ብለዋል፡፡ በድረ ገፅ የሚጠቀሙ ያጋጠማቸው ችግር አሁን ሙሉ በሙሉ የተቃለለ በመሆኑ ተፈታኞቹ ውጤታቸውን በተቋሙ ድረ ገፅ በ www.nae.gov.et አሁን ጀምረው ማየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በአጭር ስልክ መልዕክት የሚጠቀሙ መጨናነቁ አሁን እየተቃለለ በመሆኑ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡ የአጭር መልዕክቱን rtn ብለው ከፃፉ በኋላ የመፈተኛ የመለያ ቁጥር በማስገባት