ለአክሲዮን ማህበራት የትርፍ ክፍፍል ግብር አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአክሲዮን ማህበራት የትርፍ ክፍፍል ግብርን አስመልክቶ አዲስ የአፈፃፃም መመሪያ ተግባራዊ ሆነ። አዲሱ መመሪያ የትርፍ ክፍፍል ሳይደረግ በአክሲዮን ባለድርሻዎች ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲውል በቃለ ጉባኤ ከተወሰነ እና ይህንንም በህጋዊ መንገድ ማረጋገጥ ከተቻለ ከትርፍ ክፍፍል ታክስ ነፃ ያደርጋቸዋል መመሪያው ። በመመሪያው መሰረት በሰነዶች ማረጋጋጫና በንግድ ሚኒስቴር ሳይረጋገጥ ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ውሏል የሚል ምክንያት ቦታ የሌለው ሲሆን ፥ የትርፍ ክፍፍሉም እንደተፈፀመ ታሳቢ ተደርጎ 10 በመቶ የትርፍ ክፍፍል ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል ነው ያለው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን። ከሀምሌ 30 ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ መመሪያ ዙሪያ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ዛሬ ተወያይቷል። የቀደሞው ንግድ ህግ ክፍተቶች በ19 94 ዓ.ም የወጣው የንግድ ህግ ላይ ማንኛውም የአክሲዮን እና ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በየዓመቱ ከሚያገኘው ትርፍ እና ለአባላቱ ከሚያከፋፍለው ትርፍ ውስጥ 10 በመቶ ግብር እንዲከፍል ይደነግጋል። ይህን ህግ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረጉ በኩል በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የትርፍ ክፍፍል ግብሩንም እያሳወቀ በመክፈል ረገድ በንግዱ ማህበረሰብ በኩል በነበረው ክፍተት በሚገባ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል ። ህጉ የኩባንያዎቹ ትርፍ ለአባላት ሲከፋፈል ግብር እንደሚከፈል ይገልፃል ። አብዛኛዎቹ የንግዱ ማህበረሰብ አባለት ደግሞ ይህን ትርፍ ለአባላቶቻችን እስካላከፋፈልን ድረስ የ10 በመቶ ግብርን መክፈል እንደማይገደዱ በመግለፅ ለካፒታል ማስፋፊያ አውለነዋል የሚል ምክንያት የሚያቀርቡበት ሁኔታ ነበር ። የለም ኩባንያዎቹ አመ