Written by ዮሐንስ ሰ. ግን ደንታችን አይደለም፤ ነጋዴዎችን ከማውገዝ ለአፍታም አንቆጠብም! ታዋቂዋ የኢኮኖሚክስ ምሁር ዶ/ር ኢሌኒ ገብረመድህን በእህል ገበያ ዙሪያ ከ20 አመት በፊት ባደረጉት ሰፊ ጥናት የተገኘውን ውጤት በድጋሚ የሚያረጋግጥ አዲስ ጥናት ሰሞኑን በተካሄደው የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ኮንፈረንስ ላይ ቀርቧል። ከጥናቶቹ ውስጥ ጎልቶ የሚታይ አንድ ሃቅ ቢኖር፣ በእህል ገበያ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና ደላሎች በየፊናቸው ወይም ተመካክረው እንዳሻቸው የዋጋ ንረትን እንደማይፈጥሩ ነው። እንዲያውም፣ ነጋዴዎች የዋጋ ንረትን የሚፈጥርና ጉዳት የሚያደርስ ቅንጣት ያህል አቅም እንደሌላቸው ጥናቶቹ ያስረዳሉ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብና መረጃ የማይዋጥላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን፣ ከገበሬ እህል ገዝቶ የሚያመጣ ነጋዴ ከደላላ ጋር ሆኖ፣ ያሰኘውን ያህል ዋጋ እየጨማመረ በሰፊ ልዩነት የሚሸጥ ይመስላቸዋል። ከገበሬ የሚገዛበት ዋጋ ከወለል በታች በጣም ዝቅተኛ፣ ለሸማች የሚሸጥበት ዋጋ ደግሞ ከጣሪያ በላይ ከፍተኛ ነው ብለው ያምናሉ። ነጋዴው በሰፊ የዋጋ ልዩነት እጥፍ ሲያተርፍ፣ ከዚያም አልፎ የእጥፍ እጥፍ ዋጋ እየጨመረ ትርፍ ሲዝቅ በምናብ ይታያቸዋል። በተጨባጭ መረጃዎች እና በዝርዝር ጥናቶች ተደጋግሞ የተረጋገጠው እውነታ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ነጋዴዎች ከገበሬ እህል የሚረከቡበት ዋጋ እና ለሸማች የሚሸጡበት ዋጋ ሲነፃፀር፣ በሁለቱም መካከል ሰፊ ልዩነት እንደሌለ ጥናቶቹ ከመግለፃቸውም በተጨማሪ፣ የዋጋ ልዩነቱ ከአመት አመት በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን ያስረዳሉ። ታዲያ በእነዚህ ጥናቶችና መረጃዎች ምክንያት የአብዛኛው ሰው አስተሳሰብ የሚቀየርና በነጋዴዎች ላይ የሚሰነዘረው ውግዘት የሚረግብ እንዳይመስላችሁ። ቀድሞውንም፣ በጥናቶችና በመረጃዎች እጦት አይደ