Posts

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል 960 የግብይት ማዕከላት አዲስ ግንባታናየማጠናከር ስራ ተከናወነ

Image
ሃዋሳ ሐምሌ 19/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀዉ በጀት አመት 960 ዘመናዊ የግብርና ምርቶች ግብይት ማዕከላት አዲስ ግንባታና የማጠናከር ስራ በመከናወናቸዉ ለግብይት ስረአቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ ። በበጀት አመቱ ከክልሉ 11ሚሊዮን ያህል የቁም እንስሳትና ቆዳና ሌጦ ለገበያ መቅረቡም ተመልክቷል፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የማዕከላቱ ስራ ህገ ወጥነትን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለው የግብይት ስርዓት መፍጠር ነዉ ። ፡በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በበጀት አመቱ ከተሰሩት ከእነዚህ ማዕከላት መካከል 283 አዲስ ግንባታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 677 ደግሞ የማጠናከር ተግባራት የተካሄደላቸዉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በመንግስትና በግል ባለሀብቶች ወጪ የተከናወኑ ማእከላት እያንዳንዳቸውም ከግማሽ ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር የፈጁ መሆናቸውን አሰረድተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር በመተባበር የተሰሩት የግብይት ማዕከላቱ የጥራት ደረጃተቸውን የጠበቀ የቡና፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የጥራጥሬ፣ የቅመማ ቅመም፣ የቁም እንስሳትና ሌሎችንም የግብርና ምርቶች እየቀረቡባቸዉ መሆኑም ተመልክቷል ። ማእከላቱ በተጨማሪ መረጃዎችን በማቅረብ የአምራቹንና የሸማቹን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዙም አመልክተዋል፡፡ የግብርና ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው በአይነትና በብዛት ለገበያ እንዲቀርቡና ህገ ወጥነትን ለመከላከል ለግብይት ተዋናያዎች 3ሺህ341 አዲስ የብቃት ማረጋገጫና ለ7ሺህ269 የነባር ፈቃድ እድሳት መከናወኑም የስራ ሂደቱ ባለቤት ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች የገበያ መረጃን አሰባስቦ በማጠናቀር

በሃወሳ ከተማ ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ ያለው የማረሚያ ተቋም ግንባታ ከ90 በላይ ተጠናቀቀ

አዋሳ ሐምሌ 19/2005 የደቡብ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በሃዋሳ ከተማ ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ ያለው ዘመናዊ የማረሚያ ተቋም ግንባታ ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ገለጸ፡፡ በአስተዳደሩ ማረምና ማነፅ የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር ኑሪ ሺሾሬ እንደገለጹት የህንጻው መገንባት የህግ ታራሚዎችን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን በማረምና በማነፅ የዕውቀትና የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት በመደበው ገንዘብ የሚካሄደው ግንባታ ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የተለያዩ ሙያ ባለቤት በመሆን አምራችና ብቁ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ማዕከላዊ የማረሚያ ተቋሙ የመመገቢያ አዳራሽ፣የህክምና ክፍል፣የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ቤተመፃሕፍት፣የተለያዩ የሙያ ማስልጠኛ ማዕከል፣ መዝናኛና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ ሲሆን በሚቀጥለው የበጀት ዓመት አጋማሽ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል፡፡ የማዕከሉ መገንባት ታራሚዎች በቆይታቸው በሚያገኙት ዕውቀት በሀገሪቱ በመካሄድ ያሉ የሰላም ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ያስችላቸዋል፡፡ ማዕከሉ በክልሉ ለሚገኙ 22 የማረሚያ ተቋማት የሚያገለግል በመሆኑ በህመም ምክንያት ሪፈር የሚፃፍላቸውን ህሙማን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድም ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ከ57 ሚሊዮን ብር በሚበጥ ወጪ በወላይታ ሶዶ፣ በዲላና በሆሳዕና የማረሚያ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ስልጠና ማዕከልና ሌሎችንም በማካተት በአዲስ መልክ የመገንባት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ በሚዛን አማንና በበንሳ በተመሳሳይ አዲስ የማረሚያ ተቋማት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም ኮ

በሲዳማ ዞን ከ30 ሺህ የሚበልጡ አንቀሳቃሾች ተደራጅተው ወደ ስራ ገቡ

ሃዋሳ ሐምሌ 18/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ30 ሺህ የሚበልጡ አንቀሳቃሾችን በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ ለአንቀሳቃሾቹ ከ12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መሰራጨቱ ተገልጿል፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደበበ ተገኝ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሆነውን የአነስተኛና ጥቃቅን መስኮችን የመደገፍና የማብቃት ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ባለፉት አሰራ ሁለት ወራት 30 ሺህ 673 አንቀሳቃሾችን በተለያየ ማህበራት በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንና ከነዚህም መካከል 8 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ፡፡ መምሪያው አንቀሳቃሾቹ ጥራት ያለውን ምርት አምርተው በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል በየደረጃው የክህሎትና የቴክኖሎጂ ድጋፍን ጨምሮ ሌሎች የአቅም ግንባታ ስራዎችን በዞኑ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህም አዲስ ወደ ስራ የገቡትን ጨምሮ ከ40 ሺህ በላይ አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ አንቀሳቃሾቹ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታና በሌሎች ዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመምሪያው የድጋፍ ማዕቀፎች አፈፃፀምና ክትትል ዋና የስራ ባለቤት ወይዘሮ ሐረገወይን ኃይለሚካኤል በበኩላቸው በዘርፉ ቀደም ብሎ የሚገኙትንና በአዲስ መልክ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ አንቀሳቃሾች ስራቸውን ለመጀመርና ለማስፋፋት ከ12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር እንዲያገኙ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ የማምረቻና

በሀዋሳ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ተሰራ

አዋሳ ሐምሌ 18/2005 በሀዋሳ ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ66ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ 25 ኪሎ ሜትር መንገድ በጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መሰራቱን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገለጸ፡፡ የማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባበሪ አቶ መብራቴ መለሰ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በበጀት አመቱ መግቢያ ላይ የተጀመረው የድንጋይ ንጣፍ መንገዱ ግንባታ በእቅዱ መሰረት በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልገሎት በቅቷል፡፡ በከተማው አሰተዳደር በጀት የተገነባው የድንጋይ ንጣፉ መንገድ ስራ ሰባት ሜትር ስፋት አለው ብለዋል፡፡ ለእግረኛና ተሽከርካሪ የሚያገልግለው በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች የተገነባ በመሆኑ በዋጋ ደረጃ ከአስፓልት አንጻር ርካሽና ለረጅም አመታት አገልግሎት እንደሚሰጥ ቢበላሽ በቀላሉ መጠገን የሚቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ስራው ሰልጠነው በተደራጁ 148 ድንጋይ ጠራቢና አንጣፊ ማህበር ከስድስት ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው እያንዳንዱ ማህበራት በየቀኑ እስከ 20 ሌሎች ሰዎችን በመቅጠር ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በከተማው የአሁኑን ሳይጨምር ቀደም ብሎ የተሰራ 55 ኪሎ ሜትር የድንጋይ ንጣፍ መንገድ እንዳለ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል 17 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ደረጃውን ወደጠበቀ አስፓልት ለማሳደግ በ46 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በግል ተቋራጭ እየተካሄደ እንደሚገኝ ያስረዱት አቶ መብራቴ ይሄው መንገዱ ከነባሩ ቴሌ እሰከ አዴቬንቲስት ቤተክርስቲያን፣ ከመናሃሪያ ዋንዛ ወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይና ከአላሙራ ትምህርት ቤት ወደ ሞኖፓል አቋርጦ የሚያልፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከመንገዱ ስራ እስካሁን ግማሽ ያህሉ መከናወኑንና እሰከ መጪው መስከረም 2006 ተጠናቆ ለአገልገሎት ይበቃል ብለዋ

ሲዳማን ጨምሮ ከደቡብ ክልል ዘንድሮ ከ83 ሺህ 100 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

ሃዋሳ ሐምሌ 16/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት አመት 83 ሺህ 140 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ቡናው የቀረበው በክልሉ ቡና አምራች ከሆኑ የተለያዩ ዞኖች በሚገኙ 380 የህብረት ስራ ማህበራትና ከ330 በሚበልጡ የግል ባለሃብቶች እንዲሁም የቡና ተክል ልማት ድርጅት አማካኝነት ነው፡፡ በዘመኑ ለማዕከላዊ ገበያ ገበያ ከቀረበው ከዚሁ ቡና ውሰጥ 42 ሺህ 189 ቶን የታጠበና ቀሪው 40 ሺህ 951 ቶን ደግሞ ያልታጠበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስራው ላይም 394 የቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ክንውኑ የእቅዱን 68 በመቶ መሸፉኑንና ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ከዕቅዱ ሊያንስ የቻለው ህገ ወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር መበራካት እንዲሁም የአለም ገበያ ዋጋ መቀነስና መዋዥቅ ጋር ተያይዞ ቡና አምራቹ ገበሬና አቅራቢው ወደፊት ዋጋው ይጨምራል በሚል በክምችት መያዙ አቶ መላኩ በምክንያትነት ከጠቀሱት ውስጥ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከክልል እስከ ቀበሌ በየደረጃው የተቋቋመው የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥር አሰተባባሪ ግብረ ሀይል በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድ እንዲቆም ለማድረግ በዘመኑ በተካሄደው እንቅሰቃሴ ጀንፈል፣ መርቡሽ፣ እሸት ቡና ጨምሮ ከ21 ሺህ 700 ኩንታል በላይ ቡና ከህገ ወጦች ተይዞ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ በህጋዊ መንገድ በመሸጥ ለመንግስት ገቢ መሆኑን የስራ ሂደቱ ባለቤቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡