በክልሉ የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ ለማጠናከር ትኩረት ይሰጣል
አዋሳ ሐምሌ 07/2005 በደቡብ ክልል የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ በማጠናከር ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አዲሱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት የ2006 በበጀት ዓመት እቅድ ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በየዘርፉ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በመገምገምና መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት በቀጣይ በሁሉም የልማት መስኮች ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወንና የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ይደረጋል፡፡ በርብርቡ የሚካሄደው መንግስትና በድርጅት የቅርብ አመራር ሰጭነት፣ በባለሙያው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፈፎና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በየስራ ዘርፉ የግንባር ቀደም ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በገጠርም ሆነ በከተማ ድህነትን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ የጋራ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በክልሉ ታቅደው ላልተከናወኑ ተግባራት በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣ የአስፈፃሚውና የፈፃሚው አቅም ውስንነት፣ቴክኖሎጂውን በተሟላ ሁኔታ ያለመጠቀም በዋናነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጉድለቶችን ለመቅረፍ የመንግስት፣ የድርጅትና የዝህብ ክንፎችን አቅም አቀናጅቶ በየደረጃው የልማት ሰራዊት በመገንባት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የሚሌኒየም የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከናወኑ ገልፀዋል፡፡ በግብርናው መስክ አርሶአደሩ የተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቅሞ ምርትና ምር