ሀዋሳ ዪኒቨርስቲ ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን በቅድመና ድህረ ምረቃ ኘሮግራም ዛሬ አስመረቀ
አዋሳ ሐምሌ 06/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2006 የትምህርት ዘመን ለሚያካሄዳቸው ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 1ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ከመንግስት የተመደበለት መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ገለጹ፡፡ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸው ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞ ዛሬ አስመርቋል፡፡ በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በ2006 የትምህርት ዘመን በአራት ፕሮግራሞች ሰባት ውጤቶች ላይ በማተኮር 57 ዋና ዋና ተግባራትን ለማከናወንና 40 ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም 1ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል፡፡ ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ የህብረተስብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማካሄድ አኳያ በ2005 የበጀት አመት ከመንግስት በተመደበለት ከ975 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ማከናወኑንም አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ሰራዎች ዩኒቨርስቲው የቅበላ አቅሙን ለማሰደግና የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው አመልክተው መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተነደፈው 70 በመቶ የቴክኖሎጂና ተፈጥሮ ሳይንስ መስክና 30 በመቶ ማህበራዊ ሳይንስ ሀገራዊ የተማሪ ቁጥር ምጣኔ ሙሉ በሙሉ መተግበሩን አስታውቀዋል፡፡ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የትምህረት ዘርፎች ተግባራዊ ያደረጉት አዱሱን ተማሪ ተኮር የሞጁለር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴና ተከታታይ የተማሪዎችን ውጤት ምዘና ስርዓት አጠናክሮ በመቀጠል ከዚህ ቀደም ከትምህርታቸው ይሰናበቱ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በዘመኑ ለመማር ማስተማር የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ግብኣቶችን የማሟላትና የማደራጀት ስራዎች መከናወናቸውን ዶክተር ዮሴፍ ጠቁ