Posts

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተጀመረ የክልሉን ርዕስ መስተዳደር ሹመት ጽድቋል

Image
ከሃዋሳ በደረሰን ዜና መሰረት የቀደሞውን የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተክተው ኣቶ    ደሴ ዳልኬ  ተሹመዋል። የኣቶ ደሴ ዳልኬ መሾም ሲዳማ በደቡብ ክልል መንግስት ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሚና ትልቅነት የሚያሳይ እና በክልሉ ያለው የፖለቲካ መሪነት ቀጣይነት ያረጋገጠ ነው ተብለዋል። ሲዳማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ተዋቅሮ የነበሩት ብሄርና ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ወደውም ሆነ ሳይወዱ በኣንድ ክልል ከተጠቃለሉ ጊዜ ጀምሮ ሲዳማ የክልሉን ፖለቲካ በበላይነት መምራቱን ቀጥሎበታል። እስከ ኣሁን የደቡብ ክልልን ከመሩት እና በመምራት ካሉት ኣራት ርዕስ መስተዳደሮች መካከል ሶስቱ ከሲዳማ ናቸው። ኣቶ ደሴ ዳልኬ ባለፉት ኣስራ ሁለት ኣመታት በሲዳማ ዞን ውስጥ በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ የሰሩ እና ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የቆዩ ናቸው። የኣቶ ደሴ ዳልኬ ወደ ደቡብ ክልል ተመልሰው መምጣት ለሲዳማ ያለው እድምታ ምን እንደሆነ ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም በሲዳማ ዘንድ የተደበላለው ስሜት ፈጥሯል። ኣቶ ደሴ ዳልኬ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በየጊዜው እየተነሳ የቆየውን የሲዳማ ክልል ጥያቄን በተመለከተ የሚኖራቸውን ኣቋም ከዚህ በፊት ከነበሩት የክልሉ መሪዎች የተለየ እንደማይሆን የተገመተ ሲሆን ለክልል ጥያቄው ኣዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉ ከሆነ የሲዳማ ህዝብ ድጋፊ እና ፍቅር ሊያገኑ ይችላሉ ተብሏል።

አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆኑ

ሃዋሳ ሐምሌ 06/2005 የክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ደሴ ዳልኬን የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ርእሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ ከቀድሞው ርእስ መስተዳድር ከአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን መንግስት ቁልፍ በመረከብ በይፋ ስራ ጀምረዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ እንዳስገነዘቡት ክልሉ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማእከል በመሆኑ ለእኩል የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ፡፡ መላ የክልሉን ሕዝብ በአንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ የሲዳማ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ የትምህርት ዝግጅታቸው በስነ ህይወት ሳይንስ የመጀመሪያና በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል በተለያየ የሃላፊነት እርከን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የቀድሞው ርእስ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፉት ስምንት አመታት በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደር እንደዲሰፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ድርጅቱ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=9613&K=1

Hawassa University graduation ceremony 2005

Image
Hawassa University to hold a graduation ceremony for 2005 E.C. graduates on July 13 & 14,2013 consecutively @ Main Campus.  " Congratulation to all graduating students"

መልካም ሳምንት ለመላው ሲዳማ _ኣዱኛ ዱሞ ሃኖ

Image
ኣዱኝ ዱሞ ሃኖ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ነገ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ይሾማል

Image
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5 /2005 (ዋኢማ) -የደቡብ ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል። ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የ2005 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ያደመጠ ሲሆን ፥ በ2006 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድ ላይ በመወያየት በሙሉ ድምጽ አፅድቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት ፥ በክልሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ ይቀርብበት የነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም ታይቷል። በክልሉ ሁሉን አቀፍ የቀበሌ መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም ዝቀተኛ አፈጻጸም የታየበት ሲሆን ፥ ቀሪ ስራዎችን በጊዜ ለማጠናቀቅም ተጨማሪ ተቋራጮችን ወደ ስራ አስገብቶ እየተሰራ መሆኑም ነው በሪፖርቱ የቀረበው። ምክር ቤቱ በክልሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይ በክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አማካኝነት የቀረቡ ሪፖርቶችንና የተሰሩ ስራዎችንም አድምጧል። ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት በሚቀየው ጉባኤ የ2006 አመት በጀትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም በነገው ዕለት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እንደሚሾም ይጠበቃል  ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል ።