Posts

አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆኑ

ሃዋሳ ሐምሌ 06/2005 የክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ደሴ ዳልኬን የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ርእሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ ከቀድሞው ርእስ መስተዳድር ከአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን መንግስት ቁልፍ በመረከብ በይፋ ስራ ጀምረዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ እንዳስገነዘቡት ክልሉ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማእከል በመሆኑ ለእኩል የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ፡፡ መላ የክልሉን ሕዝብ በአንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ የሲዳማ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ የትምህርት ዝግጅታቸው በስነ ህይወት ሳይንስ የመጀመሪያና በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል በተለያየ የሃላፊነት እርከን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የቀድሞው ርእስ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፉት ስምንት አመታት በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደር እንደዲሰፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ድርጅቱ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=9613&K=1

Hawassa University graduation ceremony 2005

Image
Hawassa University to hold a graduation ceremony for 2005 E.C. graduates on July 13 & 14,2013 consecutively @ Main Campus.  " Congratulation to all graduating students"

መልካም ሳምንት ለመላው ሲዳማ _ኣዱኛ ዱሞ ሃኖ

Image
ኣዱኝ ዱሞ ሃኖ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ነገ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ይሾማል

Image
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5 /2005 (ዋኢማ) -የደቡብ ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል። ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የ2005 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ያደመጠ ሲሆን ፥ በ2006 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድ ላይ በመወያየት በሙሉ ድምጽ አፅድቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት ፥ በክልሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ ይቀርብበት የነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም ታይቷል። በክልሉ ሁሉን አቀፍ የቀበሌ መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም ዝቀተኛ አፈጻጸም የታየበት ሲሆን ፥ ቀሪ ስራዎችን በጊዜ ለማጠናቀቅም ተጨማሪ ተቋራጮችን ወደ ስራ አስገብቶ እየተሰራ መሆኑም ነው በሪፖርቱ የቀረበው። ምክር ቤቱ በክልሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይ በክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አማካኝነት የቀረቡ ሪፖርቶችንና የተሰሩ ስራዎችንም አድምጧል። ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት በሚቀየው ጉባኤ የ2006 አመት በጀትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም በነገው ዕለት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እንደሚሾም ይጠበቃል  ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል ።

ከሐዋሳ እስከ ሞጆ ለሚገባው የኤክስፕረስ መንገድ ከደቡብ ኮሪያ ብድር ተገኘ

Image
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2005(ዋኢማ) - ኢትዮጵያ ከሐዋሳ ወደ ሞጆ ለሚወስደው ፈጣን (ኤክሰፕረስ)መንገድ ግንባታ ከደቡብ ኮሪያ የጠየቀችውን 700 ሚሊዮን ዶላር ብድር በአፋጣኝ እንዲለቀቅ የአገሪቱ ፓርላማው አፈ ጉባዔ ግፊት እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠየቁ።  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ካንግ ቻንግ ሂ የተመራውን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት እንዳሉት በሁለቱ አገሮች መካከል በደም የተሳሰረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢኮኖሚና በንግድ መስኮችም ማጠናከር አስፈላጊ ነው።  ደቡብ ኮሪያ በቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል ረገድ ያላትን ሰፊ አቅም በመጠቀም በቴክኖሎጂና በዕውቀት ሽግግር ለኢትዮጵያ የሚቻላትን ትብብር እንድታደርግ ጠይቀዋል። አቶ ኃይለማርያም ከሐዋሳ ወደ ሞጆ ለሚወስደው ፈጣን መንገድ ወይም ኤክሰፕረስ መንገድ ግንባታና የኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ የጠየቀችው ገንዘብ በፍጥነት እንዲለቀቅ የፓርላማው አፈ ጉባዔ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።  ከደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ብድር አነስተኛ ወለድና በረዥም ጊዜ የሚከፈልበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉ የአገሪቱ ፓርላማ የግፊትና የማግባባት ጥረት እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል። አቶ ኃይለማርያም የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጊሁን ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስያና ኦሽንያ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አረጋ ኃይሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።  የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ካንግ ቻንግ ሂ በበኩላቸው በሁለቱ አገሮች ምክር ቤቶች መ

በወንዶገነት፣ በይርጋዓለም፣ በአለታ ወንዶና በጩኮ ከተሞች ነዋሪ የሆኑት ...

Image
ቁጠባ የታደጋቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚገኙ አራት ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል የአንዳንዶቹን ኢኮኖሚ አቅም የማጠናከሩ ሥራ ፍሬያማ ውጤት አስገኝቷል፡፡ በወንዶገነት፣ በይርጋዓለም፣ በአለታ ወንዶና በጩኮ ከተሞች ነዋሪ የሆኑት የእነዚህ ወገኖች ኢኮኖሚ አቅም ሊያንሰራራ የቻለው በቁጠባ ላይ መሠረት ያደረገ ሥልጠና ተሰጥቷቸው በራስ አገዝ የቁጠባ ቡድን እንዲደራጁ፣ ቁጠባ እንዲጀምሩና በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ በመደረጉ ነው፡፡  በዚህ መልኩ ከተንቀሳቀሱት ወገኖች መካከል በአለታ ወንዶ ከተማ ልዩ ስሙ ዲላ ሠፈር ነዋሪ የሆነው ባሕሩ አወቀ ይገኝበታል፡፡ ባሕሩ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፣ እናቱንና የባለቤቱን እህት ጨምሮ የስድስት ቤተሰቦች አስተዳዳሪ ነው፡፡ “እኔ፣ ባለቤቴና ሌሎች ሁለት ጐረቤቶቼ ሆነን በሳምንት አሥር ብር መቆጠብ ጀመርን፡፡ ቁጠባችን እያደገ መጥቶ ከላዩ ላይ 300 ብር አንስቼ ብስክሌት ገዛሁና ማከራየት ጀመርኩ፤” ይላል፡፡  ከዚህም የሚያገኘውን ገቢ አጠራቅሞ መኖሪያ ቤቱ ደጃፍ አነስተኛ የሸቀጣሸቀጥ መደብር ከፍቶ ቀስ በቀስም የቁም ከብት የማደለብ፣ እንዲሁም በግልና በጋራ የከተማ ግብርና ሥራዎችን እንደተያያዘውና በአሁኑ ጊዜም ከ100 ሺሕ ብር በላይ በባንክ ተቀማጭ እንዳለውም አልሸሸገም፡፡  ከዚሁ ከተማ በሸመታና በጉልት ችርቻሮ ኑሮአቸውን ይመሩ የነበሩ 23 ሴቶችም በየወሩ ሦስት ብር፣ ከዛም አሥር ብር በባንክ መቆጠብ እንደጀመሩ፣ ቁጠባቸውም ወደ 260 ብር ከፍ እንዳለና ይህንኑ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው በመቀጠል የቁጠባ መጠናቸው ወደ 15 ሺሕ ብር፣ ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ 34 ሺሕ ብር ከፍ እንዳለ ለማወቅ

ታላቋ የአፍሪካ መዲና ከትንሿ ሸበዲኖ ምን ትማር?

Image
የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ አለም አቀፋዊ ድርጅቶች መናኸሪያ ነች፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች መሄዷ ቢነገርላትም በፅዳትና በንፅህናዋ ረገድ ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ዋና ዋና የከተማይቱ ጎዳናዎችና ትላልቅ አደባባዮች ሳይቀሩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ዋጋ የማይከፈልባቸው መፀዳጃ ቦታዎች በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ እዚህም እዚያም እየተንጠባጠቡ የሚታዩትን እዳሪዎችን ላለመርገጥ እየዘለሉ መራመድ በብዙ የከተማዋ አካባቢዎች የተለመደ ተግባራት ናቸው፡፡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደሚኖርባት በሚነገርላት በዚህችው ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች አንድና ሁለት ተብለው የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ በማህበር ተደራጁ ለተባሉ ቡድኖች ተሰጥተው ለተጠቃሚው አገልግሎት የሚሰጡት ገንዘብ እየተከፈለባቸው ሆኗል፡፡ ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎቱ ገንዘብ የመክፈል አቅም የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎችና ከተማዋን በአግባቡ የማያውቁ እንግዳ መንገደኞች የተፈጥሮ ጥሪን የመመለስ ግዴታ አለባቸውና እዳሪያቸውን በመንገዱና በየአደባባዩ ለመውጣት ይገደዳሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በከተማዋ እጅግ የተለመደና እንደ ባህል ሆኖ የኖረው ጉዳይ ነው፡፡ “ሐበሻ መንገድ ላይ ሲበላ እንጂ ሲፀዳዳ አያፍርም” እየተባለ ሲተረትበትም ኖሯል፡፡ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት፣ ንጉሱ ህዝቡ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እንዲቆጠብ የሚያሳስብ አዋጅ አስነግረው የመፀዳጃ ቤትን ጠቀሜታ ለህዝባቸው ለማስተማር ጥረት አድርገው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ በአፄ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስታት ሲከናወን የቆየ ተግባር ነው፡፡ የህዝብ የመፀዳጃ ቤቶች በከተማው ዋና ዋና ስፍራዎች ላይ እንዲገነቡ ተደርገው ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ህብረተሰቡ ከመፀዳጃ ቤት ው