በሀዋሳ ከተማ ዘንድሮ ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆኑ
አዋሳ ሰኔ 24/2005 በሀዋሳ ከተማ በዘንድሮ የበጀት አመት ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ድጋፍ ማዕቀፍ አፈጻጸምና ክትትል ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኤፍሬም አለማየሁ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወጣቶችና ሴቶች የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት በማኒፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎትና በንግድ ስራ ዘርፎች ተደራጅተው በተደረገላቸው ሁለገብ ድጋፍ ነው፡፡ ከተጠቃሚዎች መካከል 11ሺህ 612 ሴቶች መሆናቸውን አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡ የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት እነዚሁ ወጣቶችና ሴቶች ከ17 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ እንዲቆጥቡ መደረጉንም አመልክተዋል፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና የስራ ሂደት አሰተባባሪ አቶ ውቤ ቤላሞ በበኩላቸው ከ18 ሺህ 600 ለሚበልጡ አንቀሳቃሾች የንግድ ስራ አመራር፣ የቴክኒክ ሙያ ፣ የምክር አገልገሎት፣ የተስማሚ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ድጋፍ መሰጠቱን ጠቁመው ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ በመከፋፈል እንዲጠናከሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ለሌሎች 7 ሺህ 772 አንቀሳቃሾች ደግሞ ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስሰርና ገቢ እንዲያገኙ መደረጉን በመምሪያ የማምረቻ ማዕከላት ግንባታ ማስተዳደርና የገበያ ልማት ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አብርሀም አስረድተዋል፡፡ የተፈጠረው የገበያ ትስሰርና ገቢውን ያገኙት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ባዛርና አውደርኢ በማዘጋጀት፣ በኮብል ስቶንና በሌሎችም የግንባታ ስራዎች ቅድሚያ ዕድል እንዲያገኙ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም 18 ሺህ 526 ካሬ