የሐዋሳ ስታዲየም ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል
የስታዲየሙ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 23 በመቶ ያህል የተጠናቀቀ ሲሆን ከተያዘለት የጊዜ ገደብ አስቀድሞ እንዲጠናቀቅ ሥራው እየተፋጠነ ይገኛል፤ በቀድሞ አጠራሩ « ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ስታዲየም » በአሁኑ ደግሞ « አዲስ አበባ ስቴዲየም » የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና ለሆነችው አዲስ አበባ የአገሪቱንና የክለቦችን ዓለም አቀፍ ውድድሮች የምታስተናግድበት ብቸኛው ስፍራ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ሠላሳ አምስት ሺ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም እንዳለው የሚነገርለት የአዲስ አበባ ስቴዲየም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 1940 እንደተገነባ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። ስታዲየሙ በአውሮፓውያኑ 1962 ፣ 1968 ና 1976 የተካሄዱ ሦስት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ተስተናግደውበታል። ኢትዮጵያ ካስተናገደቻቸው ከእነዚህ ሦስት የአፍሪካ ዋንጫዎች መካከል ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባለድልም ሆናበታለች። አዲስ አበባ ስታዲየም የአፍሪካ የወጣቶች ሻምፒዮናና 16 ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናም በብቃት ተስተናግደውበታል። ይህ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠረውና በመዲናዋ በብቸኝነት ደከመኝ ሰለችኝ ሳይል ከአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች በተጨማሪ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱበት ስታዲየም « አንድ ለእናቱ » እየተባለ የሚጠራበት ጊዜ ማብቂያ የተቃረበ ይመስላል። ለዚህ ማሳያው ደግሞ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በባሕር ዳር፣ በመቀሌ፣ በነቀምትና በሐዋሳ ከተሞች በመገንባት ላይ የሚገኙት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእነዚህ ስታዲየሞች መካከል ግንባታው ከተጀመረ የአንድ ዓመት እድሜ ያስቆጠረው የሐዋሳ ስታዲየም ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል። የጋዜ