አንድነት በአገር ጥቅም ላይ ከማንም ጋር እንደማይደራደር አስታወቀ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መንግስትና ገዢው ፓርቲ የአገሪቷን ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀማቸው አገርን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ገለፀ፡፡ ከትላንት በስቲያ ፓርቲው በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “የኢህአዴግን ስርዓት ከቀደሙት አምባገነን ስርዓቶች ለየት የሚያደርገው ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ስልጣን መጠቀሚያ ማዋሉ ነው” ያለው አንድነት፤ ከዚህም ውስጥ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አንዱ እንደሆነ ገልፃል፡፡ ግድቡ ከመጀመሩ በፊት ማለቅ የነበረባቸው ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ነበሩ፣ ግድቡን ከፓርቲ አጀንዳ ወደ ህዝብ አጀንዳነት ማውረድ አለበት፣ የግድቡ ስራ አንድ አካል የሆነውን የወንዝ አቅጣጫ ማስቀየር በግንቦት ሀያ ዕለት ማድረጉ ፖለቲካዊ እንጂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የለውም፣ ያለው አንድነት ፓርቲ፤ መንግስት ለግድቡ ግንባታ ከጉሮሮው እየነጠቀ የሚወስደው ከህዝብ ስለሆነ የአባይ ግድብ ጉዳይ የህዝብ አጀንዳ እንዲሆን መንግስት ከተቃዋሚዎችም ሆነ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር አገራዊ ውይይና መግባባት ላይ መድረስ እንዳለበት ፓርቲው በመግለጫው አሳስቧል፡፡ “የአንድ መንግስት ግዴታዎች የሆኑት ተግባራት መንገድ ውሃ፣መብራትና መሰል ተግባራት መዳረሻቸው የፖለቲካ ስልጣን ማራዘም ነው ያለው ፣ለፖለቲካ ፍጆታ የማይውል ንፁህ መሰረተ ልማት ወሳኝ መሆኑን ፓርቲው በፅኑእንደሚያምን ገልፆ ዛሬ እንደ አዲስ ኢህአዴግ ያነሰው በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ መስራትና ማልማት አስፈላጊነት ለዘመናት ሲነሳ የነበረ ጉዳይ እንደሆነም አስታውሷል፡፡ የአባይን ጉዳይ በተመለከተ ከአንድ አመት የተመረጡት የግብፅ ፕሬዝዳንት መሀመድ ሙርሲ ሃሳባቸው ተቀባይነት ይኑረውም አይኑረውም ከተቃዋሚዎች ጋር እንደተነጋገሩ የሱዳን መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን በመፍ