መንግሥት ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ
የግብፅ ፖለቲከኞች ከአፍራሽ ድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል የግብፅ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ባለፈው ሰኞ በተካሄደው ብሔራዊ የናይል ኮንፈረንስ ላይ ታላቁን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ በተንፀባረቀው አፍራሽ መልዕክት የተበሳጨው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም” ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ የግብፅ ፖለቲከኞችም ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡ የግብፅ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትሮችና የፀጥታ ባለሥልጣናት በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ፣ “የህዳሴ ግድቡ በግብፅ ላይ አደጋ በመደቀኑ በኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ መንገዶች ተፅዕኖ በመፍጠር የግድቡን ሥራ ለማስቆም እንቅስቃሴ እናደርጋለን፤” በማለታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት “አፍራሽ ድርጊት” በማለት አጣጥሎታል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነበር የመንግሥትን አቋም ግልጽ ያደረጉት፡፡ “በህዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረት የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አያስጠብቅም፤” ያሉት አምባሳደር ዲና፣ “ጦርነቶችና ሌሎች አፍራሽ ድርጊቶች ያረጁና ያፈጁ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከማቸው ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች ናቸው፤” በማለት የግብፅ ባለሥልጣናትን ድርጊት አጣጥለውታል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለአንዲት ሰከንድም ቢሆን እንደማታቆም አረጋግጠዋል፡፡ “የግብፅ ወገኖችም ከዚህ አፍራሽ ድርጊት እንዲቆጠቡ፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ “የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ መንግሥት እየያዘው ባለው መንገድ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠራ ነው ወይ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ መንግሥት አስፈ