ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ
አዋሳ ግንቦት 30/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከሁሉም የትምህርትና የምርምር ዘርፎቹ ጋር አቀናጅቶ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሰቲው ተማሪዎችና መምህራን አለም አቀፍ የአካባቢ ቀን በችግኝ ተከላ፣ በጽዳት ዘመቻ፣ በእግር ጉዞና በፓናል ውይይት ትናንት በሀዋሳ ከተማ አክብረዋል፡፡ በበዓሉ ላይ ዩኒቨርስቲው የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዶክተር ንጋቱ ረጋሳ እንደገለጹት ተፈጥሮን በመንከባከብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በዕወቀት ላይ የተመሰረተና ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ጥበቃና ልማት ወሳኝ ነው፡፡ ዪኒቨርስቲው በዚህ ረገድ በተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ በርካታ የምርምር ፕሮግራሞች በግብርናው ዘርፍ እንዳሉት ጠቁመው ይህንን ከሁሉም የትምህርትና የምርምር መስኮች ጋር አቀናጅቶና አስፋፍቶ ለመስራት ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ እያንዳንዱ ዲፓርትመንት ስርዓተ ትምርህርት ሲቀርጽ የአካባቢን ጥበቃ ጉዳይ ግምት ውስጥ በማስገባት መስራት እንዳለበት ፕሮፌሰር ንጋቱ ገልጸው በተማሪዎችና በመምህራን የተቋቋመው የአካባቢ ጥበቃ ክለብ ተጠናክሮ ሁሉንም ማህበረሰብ በማሳተፍ እንዲቀሳቀስ ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በአካባቢ ላይ የሚሰሩ ምርምሮችን ዩኒቨርስቲው ያበረታታል ያሉት ፕሮፌሰሩ የአካባቢው ህብረተስብ ስለጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማጎልበት በማህበረሰብ ሬዲዮ ጭምር በመጠቀም እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም ከክልሉ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነታቸውን አጠናክረው ህዝቡም ከትምህርትና ምርምር ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እሰሩ መሆናቸውን ገልጠዋል፡፡ ዘንድሮ በሀገሪቱ ለ20ኛ በአለም ለ40ኛ ጊዜ የተከበረው የአካባቢ ቀን "አሰብ ፣ተጠ