በአንድ ቀን 14 ሠርግ ያስተናገደው ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል አሁን ባለ 5 ኮከብ ሆነ
ባለ 17 ፎቅ ሕንፃ የእንስሳት ማቆያ ዙና ሪዞርት እያሰቡ ነው እንኳን ንግድ ገበያ ወጥተው የማያውቁ የተሟላ ትዳር የነበራቸው የቤት እመቤት ነበሩ፡፡ ባለቤታቸው ወታደር ስለነበሩ፣ መኖሪያቸው ካምፕ ውስጥ ነበር፡፡ የትዳር ጓደኛቸውን ሞት ሲወስድባቸው የሚይዙትንና የሚሆኑትን አጡ፤ ሰማይ የተደፋባቸው፣ ምድር የከዳቸው ያህል ክው አሉ፡፡ ቤት ውስጥ ምንም ስላልነበር፣ በላይ በላይ የተወለዱ አምስት ሕፃናት ያለ አባት ማሳደግ እጅግ ከብዶ ታያቸው፡፡ “ምኔን አብልቼ ነው የማሳድጋቸው? እንደፈለጋቸው ይሁኑ፤” … ብለው ሜዳ ላይ በትነዋቸው አልጠፉም፡፡ ለልጆቻቸው ያሏቸው ብቸኛ ወላጅ እሳቸው ብቻ ስለሆኑ እንደምንም ለማሳደግ ወሰኑ፡፡ ባለቤታቸው በሕይወት እያሉ ለቤተሰቡ ቀለብ የተሸመተ 25 ኪሎ ዱቄት ነበር፡፡ “ይኼ ዱቄት ካለቀ ልጆቼን ምን ላቃምሳቸው ነው? አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ” ብለው አሰቡ፡፡ ያቺን ዱቄት እየጋገሩ ሽሮ ወጥ ሠርተው ምግብ ቤት ለመክፈት ወሰኑ፡፡ መኖሪያቸው ካምፕ ውስጥ ስለነበር፣ እዚያ ያሰቡትን ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ያውቃሉ። ስለዚህ ከዚያ ወጥተው ቤት ለመከራየት ወሰኑ፡፡ የሚያውቋቸው ሰዎችና ጐረቤቶቻቸው ውሳኔያቸውን አልደገፉትም። “እንዴት የሞቀ ቤትሽን ለቀሽ ትወጫለሽ? ልጆቹን ያለ መጠጊያ ልታስቀሪ ነው ወይ? ተይ! እነዚህን ሕፃናት ይዘሽ የባሰ ችግር ውስጥ እንዳትወድቂ …” በማለት መከሯቸው፣ ገሰጿቸው፡፡ እሳቸው ግን በልባቸው “ቤቴንና አቅሜን የማውቀው እኔ ነኝ፤ ይህንን ቤት እኔ አልሠራሁት፤ ደግሞም ቤቴ ውስጥ የሚሸጥም ሆነ የምግደረደርበት ንብረት የለም” በማለት ምክርና ግሳፄውን ችላ አሉት፡፡ ከዚያም ከካምፑ ወጥተው፣ የቤት ኪራይ ረከሰ ወዳለበት አካባቢ ሄደው የ8 ብር የቀበሌ ቤት ተከራዩ፡፡ “እሷንም ተጫርቼና 4 ብር ጨ