የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኪሳራው እንዲከፈለው ጠየቀ
አለመግባባት የሚያጦዘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ - የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኪሳራው እንዲከፈለው ጠየቀ - ‹‹ነገሩ ግልፅ እንዲሆንልኝ መነጋገር እፈልጋለሁ›› እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከእንቅልፉ ተነሳ ሲባል መልሶ እያንቀላፋ፣ ተነቃቃ ሲባል እየደከመው ከረጅም ዓመታት በኋላ የለውጥ ጭላንጭል የታየበት ቢመስልም፣ ጊዜና ወቅት እየጠበቀ በሚፈጠር አለመግባባት እንደገና ወደ ጡዘት የሚያስገባ ምልክት እየተስተዋለበት ነው፡፡ የእግር ኳሱን ፋና የሚያጨልም ሰው (ጓዳ) ሠራሽ ቢሮክራሲ የበላይነት፣ የሥልጣን ማሳያ ሽኩቻ፣ ያለመግባባት ፍጥጫ ቀዝቃዛ ውኃ ሲቸልስበት ኖሯል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች አሁንም እግር ኳሱ ቀና ቀና ማለት በጀመረበት ቅጽበት እንኳ የተቀየሩና የቀሩ አልመስል እያሉ ጉዞውን አስቸጋሪ እያደረጉበት ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ የሚታየው ውዝግብም ኳሱ ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ለዓመታት ተገልሎ የቆየበት ምክንየት ምን ነበር? የነበረውን ችግር ከሥር መሠረቱ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ምንድነው? ዛሬስ ከዓመታት መገለል በኋላ ምን ዓይነት ለውጥና ዕድገት አምጥቶ ነው መድረኩን የተቀላቀለው? በሚሉትና ሌሎችም ተመሳሳይ የችግር አፈታት ሒደቶች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ የሥልጣን ድርሻና የበላይነት ላይ የተመሠረተ ሆኖ መታየቱ መንግሥትንም የሚያስተቸው መሆኑ አልቀረም፡፡ መንግሥት ‹‹ዘርፉ ከፖለቲካው ጨዋታ ውጭ እስከሆነ ድረስ ምንም ቢፈጠር ዝምታን ይመርጣል›› የሚለው የብዙዎች ትችት ወደ ኳሱም አካባቢ እየተዛመተ ስለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ እነዚሁ አካላት መንግሥት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እያከናወነ ካለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክንውኖች ስፖርቱን