Posts

ሲዳማን ጨምሮ በመላው ኣገሪቱ ስለምርጫው አጠቃላይ ሂደት ገለፃ ሊደረግ ነው

Image
ሚያዝያ 6 እና 13 ለሚካሄደው የአካባቢ፣ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ምክር  ቤቶች ምርጫን አስመልክቶ    መጋቢት 27/2005 ስለምርጫው አጠቃላይ ሂደት በየምርጫ ጣቢያው ገለፃ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ የቦርዱ የህዝብ ግኑኙነት ምክትል ሃላፊ አቶ ይስማው ጅሩ  ሕብረተሰቡ በምርጫው ዕለት መደናገር እንዳይፈጠርበት በድምፅ አሰጣጡ ዙርያ ከወዲሁ ግንዛቤ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ምርጫው የሚጀመርበትንና የሚጠናቀቅበትን ሰዓት፣ በምርጫው ዕለት መራጮች ምን ማድረግ እንደሚገባቸውና ሌሎች ለድምፅ አሰጣጡ የሚያግዙ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዲያገኙም ገለፃው አስፈላጊ ነው ያሉት ሃላፊው ሕብረተሰቡም በስፍራው በመገኘት አጠቃላይ ሁኔታውን በመረዳት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድምጽ እንዲሰጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የሚዲያ ባለሞያዎች ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን ቁልፍና ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ቦርዱ ገልጿል፡፡ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግኑኙነት ምክትል ሃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ምርጫው የተሳካ እንዲሆን የሚዲያ ባለሞያዎች የወጡትን የምርጫ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስፈፀም ረገድ ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡ ሚያዚያ ስድስት ለሚጀመረው የከተማና የአካባቢ ምርጫ የሚሆን ቁሳቁስ አዲስ አበባን ሳይጨምር ለሁሉም ክልሎች መዳረሱን ቦርዱ ጠቁሟል ሲል ኢዜአ ዘገቧል፡፡

ሲዳማን ጨምሮ የሸማቾችን ቅሬታ የሚሰብሰብ የነጻ የስልክ መስመር በስራ ላይ ዋለ

Image
የንግድ አሰራርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የሸማቹን ህብረተሰብ ቅሬታ ለመሰብሰብ የሚያስችል አዲስ የነጻ የስልክ መስመር ጥሪ በስራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ የሸማቾች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ግርማ አለማር መጋቢት 26/2005 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ የሸማቹን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዳ 8478 የመስመር ቁጥር  ያለው ነጻ ጥሪ ከመጋቢት 26/2005 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል ብለዋል፡፡   ይህም በአገሪቱ በማንኛውም አካባቢ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የንግድ ስርዓቱ በህግ አግባበ ለመዳኘት የሚሰራውን ስራ ለማጠናከር እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡ መስመሩ በአንድ ጊዜ አራት ጥሪዎችን መቀበል የሚያስችል ሲሆን ህብረተሰቡም በነጻ የስልክ መስመሩ በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰትና የጸረ ንግድ ውድድር ተግባራት ሲፈጸም ጥቆማ ለማድረስ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ሸማቹን ለጤና መታወክ የሚዳርጉ ምርቶች በገበያ ሲያጋጥማቸው በነጻ የስልክ መስመሩ ለባለስልጣኑ ቢጠቀሙ ተገቢውን ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል፡፡ ምንጭ ፋና ብሮድካስት

መከላከያ ሐዋሳ ከነማን 2 ለ0 አሸነፈ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መከላከያ ሐዋሳ ከነማን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡ መጋቢት 26/2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያና ሃዋሳ ከነማ ባካሄዱት ጨዋታ መከላከያ መድሃኔ ታደሰ እና በዳሶ ሆራ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የሐዋሳ ከነማ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በስነ ምግባር ግድፈት ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል፡፡ መከላከያ በማሸነፉ በ22 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ በአምስተኛ ደረጃ ይገኛል፡፡ ደደቢት በ27፣ ሐዋሳ ከነማ በ25፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ24፣ ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ  ፕሪምየር  ሊግ  መለስ  ዋንጫ  የ 2005 ዓ . ም  የደረጃ  ሰንጠረዥ ተ . ቁ ክለብ ተጫወተ አሸነፈ አቻ ተሸነፈ ነጥብ 1 ደደቢት 13 8 3 2 27 2 ሀዋሳ  ከነማ 13 8 1 3 25 3 ቅዱስ ጊዮርጊስ 13 6 6 1 24 4 ኢትዮጵያ ቡና 12 6 4 2 22 5 መከላከያ 13 6 4 3 22 6 መብራት ሀይል 12 4 5 3 17 7 ሀረር ቢራ 13 4 6 3 17 8 አርባ ምንጭ ከነማ 13 4 5 4 17 9 መድህን 12 4 5 3 17 10 ሲዳማ ቡና 12 2 8 2 14 11 ንግድ ባንክ 12 2 5 5 11 12 አዳማ ከተማ 13 1 4 6 10 13 ሙገር 13 0 7 6 7 14 ውሃ ስራዎች 12 0 2 10 2

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት ፍጥነት ጨምሯል ቢልም ደንበኞች ብሶበታል እያሉ ነው

•    የሞባይል ስልክ ጥራት መጓደል ምሬት እየፈጠረ ነው ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ በኢንተርኔት አገልግሎት ግንኙነት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ሙሉ ለሙሉ መፈታቱን ቢገልጽም፣ አሁንም የኢንተርኔት አገልግሎት የጥራት መጓደል እየባሰበት መሆኑን ደንበኞች አስታወቁ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ በኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት ላይ ይደርስ የነበረው ችግር የተፈጠረው በባህር ጠለቅ የፋይበር ኬብል መስመር ላይ በደረሰ ከፍተኛ ብልሽት ሳቢያ እንደሆነ መጥቀሱ ይታወሳል፡፡  ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት ትናንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ በመቃለሉ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚቻል መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህንኑ የኢትዮ ቴሌኮም መግለጫ ተከትሎ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ደንበኞች ግን አሁንም የኢንትርኔት አገልግሎት ፍጥነት እንደተባለው የተስተካከለ ሳይሆን፣ እየባሰበት ነው ብለዋል፡፡ በሰሞኑ የኢንተርኔት አገልግሎት ጥራት መጓደል በርካታ ደንበኞች ሲያማርሩ እነደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይ አገልግሎታቸውን በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር ያያያዙ ተቋማት የተፈጠረው ችግር ለኪሳራ ዳርጐናል እስከማለት መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡  አሁንም ይህ ችግር እየታየ በመሆኑ በአግባቡ የሚፈለገውን አገልግሎት ለመስጠት እንዳላስቻላቸውና ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም የኢንተርኔት አገልግሎት የጥራት ደረጃውን ማሻሻል ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡  በትናንቱ የኢትዮ ቴሌኮም መግለጫ ግን አፍሪካን ከመካከለኛው ምሥራቅና እስያን ከአውሮፓ ጋር በሚያገናኘው በሜዴትራንያን ባህር ውስጥ በሚያልፈው ኦፕቲካል ፋይበር ኬብል ላይ መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ.ም. የደረሰው ጉዳት ለኢንተርኔት ኮኔክሽን ፍጥነት አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ይገልጻል፡፡ በዚህም

Second article in Gazette: Women on the Streets

Image
By MARTY NATHAN Marta Elamura and her children. •  Related story:  Marty Nathan: Interviews reveal struggles EDITOR'S NOTE: This is the second of a two-part series on street people in Hawassa, Ethiopia. The first article examined the plight of children.   We learned of Qirchu, the Beggars' Village, from a woman I'll call Miriam, whom we met in front of St. Gabriel's Church on the square in downtown Hawassa, Ethiopia.  My assistant Dagim and I had begun to interview children and women who begged on the streets of Hawassa, prompted by the stark image of homeless children sleeping in the gutters of the city's broad boulevards. Beggars have traditionally gathered on the premises of Ethiopia's Orthodox churches, where they are given food and clothes, particularly at holiday times, and are able to appeal to the parishioners on their way to services. The church reaches back to the fourth century and has a unique, Ethiopian-centered doctrine and ritual that