ኢትዮጵያና የግለሰቦች ስለላ በኢንተርኔት - ጥናት፣ ክስና ምላሽ
የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁ ሁለት አጥኝዎች ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁት ዊልያም ማርዣክ እና ሞርጋን ማርኪስ-ቧር ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ፓሪስ-ፈረንሣይ የሚገኘው ዓለምአቀፍ ቡድን ኢትዮጵያ ያንን የርቀት መከታተያ ሶፍትዌር ግለሰቦችን ለመሰለል ጉዳይ እንደምትጠቀም እንደሚያውቅ ቢገልፅም አንድ የኢትዮጵያ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባለሥልጣን የሚባለውን ክስ አስተባብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲቲዘን ላብ የሚባለው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ማዕከል ባወጣው ዘገባ መሠረት የስለላ ማልዌሩን ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሃያ አምስት ሃገሮች የሸጠው ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድኑ - አርኤስኤፍ “የኢንተርኔት ጠላቶች” ሲል ከፈረጃቸው አምስት ሃገሮችና አምስት ድንበር ዘለል ድርጅቶች አንዱ የሆነው “ጋማ ኢንተርናሽናል” የሚባል ለንደን - እንግሊዝ የሚገኝ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራና ንግድ ላይ የተሠማራ ቡድን ነው፡፡ ጋማ ኢንተርናሽናል ጋማ ኢንተርናሽናል ማልዌሩን የሠራውና የሚሸጠው ሕፃናትን የሚያማግጡና ጥቃት የሚያደርሱባቸውን፣ ሽብርተኞችንና የተደራጁ ወንጀሎችን፣ ጠላፊዎችንና ሕገወጥ የሰዎች ሽግግርን ለመከታ