ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሊያስገኝ የሚችለው ቀርከሃ
በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ሔክታር መሬት የሚሸፍን ቀርከሃ አለ ተብሎ ይታመናል፡፡ በየዓመቱም እስከ 12 ሚሊዮን ቶን የሚገመት የቀርከሃ መጠን ለተለያዩ ምርቶች ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በዘርፉ የተደረገ ጥናት ያመለክታል፡፡ ሀብቱ ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ቢውል ደግሞ ለ500 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ከ500 ሚሊዮን እስከ 700 ሚሊዮን ብር ገቢ ሊያስገኝ የሚችል ምርት በየዓመቱ ማምረት እንደሚቻል ሰሞኑን በአፍሪካ የቀርከሃ ሀብት ዙሪያ የተደረገ ዓውደ ጥናት ላይ ተጠቅሷል፡፡ ቀርከሃ በየዓመቱ በብዛት ሊበቅል የሚችል ተክል ሲሆን በአግባቡ ከተያዘና ከተጠበቀ ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በተጨማሪ ምርቱን ሳያቋርጡ ለዓመታት ማግኘት እንደሚቻል ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ቀርከሃን በመቀጠም በኢትዮጵያ የተሠሩ ሥራዎችን በተመለከተ መጋቢት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በተካሄደ ዓውደ ጥናት ላይ ማብራሪያ ቀርቦ ነበር፡፡ ዓውደ ጥናቱን አስመልክቶ በቀርከሃ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን ያቀረበው መረጃ በቀርከሃ የተሠሩ 200 ሺሕ ቤቶች ለገጠሩ ኅብረተሰብ በግልና በሰፈራ መሥራቱን ያስታውሳል፡፡ በገንዘብ ሲሰላ ሁለት ሚሊዮን ብር እንደሚጠጋም አስፍሯል፡፡ በቀርከሃ የተሠሩ 700 ሺሕ የቤት ቁሳቁስ መሣሪያዎች የተመረቱ ሲሆን፣ ከ20 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችም የሥራ ዕድል እንደተፈጠረ ያትታል፡፡ በዚሁ መረጃ መሰረት፣ 250 ሺሕ ቶን ቀርከሃ ለማገዶ መዋሉን፣ በገንዘብ ሲመዘንም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ 45 ቶን ቀርከሃ ለከብቶች መኖነት መዋሉ ከመገለጹም ባሻገር፣ በአዲስ አበባና አሶሳ የተከፈቱ ሁለት ፋብሪካዎች እስካሁን ድረስ ከ30 ሺሕ ቶን በላይ የቀርከሃ ምርትን ለተለያየ አገልግሎት ማዋላቸውም ተዘርዝሯል፡፡ የሚ