በደኢህዴን መሪነት የክልሉ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ጎልብቷል
አዋሳ፤ መጋቢት 10/2005/ዋኢማ/ - በደኢህዴን መሪነት የደቡብ ክልል ሕዝቦች በፈቃዳቸው የመሰረቱት ክልላዊ መስተጋብርና አንድነት በሀገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት መስክ ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እንዲጎለብት ጠንካራ መሰረት መጣሉን የደኢህዴንና ኢህአዴግ ሊቀመንበር ገለጹ። የደኢህዴንና ኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የደኢህዴን 8ኛ ጉባኤ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ሲጀመር እንደገለጹት፤ በክልሉ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል የነበረው መስተጋብር በጋራ መልማትና አስተማማኝ ሰላም የማረጋገጥ ፍላጎት በመሆኑ ጠንካራ ክልል እንዲመሰርቱ አስችሏል። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባሏቸው የታሪክ የስነ-ልቦናና የተለያዩ መስተጋብሮቻቸው በአንድነት በመሰረቱት ክልል በደኢህዴን አመራር ልዩነታችን ውበታችን አንድነታችን ጥንካሬያችን ሆኖ በተሃድሶ መስመር ላገኘነው ድልና ለተመዘገበው ፈጣን ልማት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል። እስከ ደኢህዴን ሰባተኛ ጉባኤ በክልሉ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት የባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት መመዝገቡ 7ኛው የድርጅቱ ጉባኤ ተከታታይ ፈጣን ዕድገት ማስመዝገብ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ይህንን ዕድገት በማስቀጠል የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማምጣት እንዳለበት ወስኖ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። ደኢህዴን የተከተለው መስመር ተከታታይና ፈጣን ልማትን ከማረጋገጥ ባሻገር የክልሉ ህዝቦች ከልማቱ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበትና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የሚያረጋግጥ መሆኑን በተግባር እንዳስመሰከረ አቶ ኃይለማሪያም አስታውቀዋል። ደኢህዴን የክልሉን ህዝቦች ከዳር እስከዳር የማንቀሳቀስ ብቃቱን በመጠቀም ልማትን ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲ በህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረጉን አስረድተዋል። ንቅናቄው በ