Posts

ከሲዳማ ዞን ባለፉት ሰባት ወራት ከ146 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ሃዋሳ መጋቢት 2/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ባለፉት ሰባት ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 146 ሚሊዮን በላይ ገቢ ሰበሰበሰ፡፡ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንደገለጹት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ገቢውን የሰበሰበሰው ከቀጥታ ታክስ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶቸ ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች፣ከተጨማሪ እሴት ታክስና ታክስ ካልሆነ ገቢዎች ነው፡፡ ባለፉት ሰባት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ13 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡ ገቢው ሊጨምር የቻለው ጽህፈት ቤቱ ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠናዎች መስጠት በመቻሉ፣ዘመናዊ የታክስና ቀረጥ መረጃ ስርዓት በመዘርጋቱና ተደራሽ ማድረግ በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡ ባለፉት ሰባት ወራት 217 አዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ግብር ስርዓቱ የገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 19 የሚሆኑት ''ሀ'' ግብር ከፋዮች እንደሆኑ ጠቁመዋል። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በይርጋለምና አለታወንዶ ከተሞች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ለማስጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸው በበጀት ዓመቱ ከ344 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰበ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን አቶ ተሻለ አሰታውቀዋል። source:  http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6247

ሚኒስቴሩ የምሽት ጉዞዎችን ሊከለክል ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል የምሽት ጉዞዎችን እንደሚከለክል የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ላይ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ለመከላከል የአጭር ጊዜ የቁጥጥርና ክትትል ስራን ለመስራት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቅቋል፡፡ ለመንገድ የትራፊክ ደህንነት አደጋ መንስኤዎች ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ፣ ህገወጥ የሌሊት ጉዞ ፣ ከተፈቀደ የሰው ቁጥር በላይ መጫን የመንገድ ህግና ስርአትን አለማክበር ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተለይ በህገወጥ የሌሊት ጉዞ ተሳታፊ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር በትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሃይለማርያም ህግና ስርአትን ተላልፈው የሚገኙ አሽከርካሪዎችን ከጥፋታቸው ለማረም የተለያዩ መንገዶችን እንጠቀማለን ብለዋል፡፡ ከክልል ከተሞች ጋር በመቀናጀት በክልል የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስና ለመከላከል የፌዴራል ፖሊሲና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች አዲስ የቁጥጥር ሰርአት እንደሚጀመር የገለፁት ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል ናቸው ፡፡ ኮሚሽነሩ ሞጆ ፣ አዳማ፣ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ ፣ ጎሀጽዮን ፣ ወሊሶ ፣ወልቂጤ፣ ደብረብርሃን፣ ደብረሲና ፣ አምቦና ነቀምቴ በዚህ ወር ቁጥጥር የሚጀመርባቸው ከተሞች እነደሆኑም ገልፀዋል፡፡ ቁጥጥርና ክትትሉ በሌሊት የትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በቀንም በሚደረጉ የትራፊክ አገልግሎት ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ የቁጥጥርና ክትትል ስራውን ለማጠናከር የተለያዩ አጋዥ ተሽከር

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ነገ የጀምራል

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 3፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን የተመደበላቸውን የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አሳሰበ። በቀጣዩ ወር በመላ ሃገሪቱ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፥ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ በይፋ ከጀመሩ ትናንት 1 ወር መድፈናቸውን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያመለክታል። ምንም እንኳን በዚህ ጊዜ ውስጥ ፓርቲዎቹ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ፕሮግራምና እቅዶቻቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የሚችሉ ቢሆንም ፥ ባለፉት ሳምንታት ያነጋገርናቸው አብዛኞቹ ፓርቲዎች ግን ምንም ዓይነት የምረጡኝ ቅስቀሳ አለማድረጋቸውን ተናግረዋል። ፓርቲዎቹና በተለያዩ መንገዶች የሚያደርጓቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች እንደተጠበቁ ሆነው ለአንድ ወር የሚቆየው እና በመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉት ቅስቀሳ ነገ ይጀምራል። ከብሮድካስት ባለስልጣን የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ከዚህ ቀደም በነበሩ ልምዶች ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን የሚመደብላቸውን የአየር ሰዓትም ሆነ የጋዜጣ አምድ አሟጦ ያለመጠቀም ችግር አለባቸው። ለአብነት ያህል እንኳን በ2002ቱ ምርጫ 23 ያህል ፓርቲዎች ከተመደበላቸው ውስጥ ግማሹን ሳይጠቀሙበት ሲቀሩ ፥ 10 ፓርቲዎች ደግሞ በኤሌክትሮኒክስም ሆነ በህትመት መገናኛ ብዙሃን የተመደበላቸውን የጋዜጣ አምድና የአየር ሰዓት ሙሉ ለሙሉ አልተጠቀሙበትም። በመሆኑም በፓርቲዎቹ በኩል ይህ ሁኔታ ሊታረም እንደሚገባው ነው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ የሚናገሩት። ሃላፊው ፓርቲዎቹ መገናኛ ብዙሃኑን ተጠቅመው መልዕክታቸውን በሚያስተላልፉበት ወቅት የምር

አነጋጋሪው የኢትዮጳያ የሰብአዊ መብቶች መርሃ ግብር

Image
አቶ እንዳልካቸው የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሰብአዊ መብትን ከ 23 ባላነሱ አንቀፆች አካቶ መያዙን አስታውሰው በተግባር ግን በተዘዋዋሪ መንገድ በህገ መንግሥት የተጠቀሱትን መብቶች የሚዳፈሩ ና የሚሸረሽሩ ሌሎች ህጎች መውጣታቸውን ይዘረዝራሉ ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መርኀ ግብር አስፈላጊ ቢሆንም ተግባራዊ ይሆናል ብለው እንደማይጠብቁ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በምህፃሩ ሰመጉ ሃላፊና የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባል አስታወቁ ። የሰመጉ ሃላፊ ና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የአመራር አባል ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ከልምድ እንደተገነዘቡት ኢትዮጵያ ውስጥ ችግሩ ህግ ማውጣት ሳይሆን በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች ተግባራዊ አለመሆናቸውና ይህንንም ተከታተሎ ማስፈፀም አለመቻሉ መሆኑን ተናግረዋል ። በተለያየ ደረጃ ውይይት የተካሄደበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መርሃ ግብር በቅርቡ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያፀድቀው ይቀርብለታል ተብሎ ይጠበቃል ። ሰነዱም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትና በሚኒስትሮች ምክርቤት ደረጃም እንደፀደቀ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል ። ምንም እንኳን መንግሥት ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት በመርሃ ግብሩ ላይ ማወያየቱን ቢገልፅም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በምህፃሩ ሰመጉ ግን ለውይይት አለመጠራቱንና የተባለው ሰነድም እንዳልደረሰው የሰመጉ ሃላፊ አቶ እንዳልካቸው ሞላ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ አባልና የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባያፈርስ ድርጅታቸው የመርሃግብሩን ሂደት በመከታተል ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። አቶ ጌታቸው ሌላው ቢቀር ሰመጉ ቢቻ

የኮንዶምኒዬም ልዩ ኮታ ለመንግስት ሰራተኞች! ልዩ ኮታው… ለፓርቲ አባላት መሆኑ ነው?

Image
ቢሆንስ ምን ችግር አለው? “ህዝብ” ናቸዋ! ችግር ቢኖረውስ የት ይደረሳል? ዝም ነው! ብዙዎቻችን ፈቅደን ያስጀመርነው አይደል! የመንግስት ሰራተኞች ከሌላው ዜጋ የበለጠ የኮንዶምኒዬም ኮታ እንደሚመደብላቸው ባለፈው ቅዳሜ እለት ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲናገሩ በጣም ነበር የገረመኝ። የመንግስት ሰራተኞች ከሌላው ዜጋ በምን ይበልጣሉ? በርካታ የፓርቲ አባላትን ስላሉበት ነው ልዩ እንክብካቤ የሚደረግላቸው? አይን ያወጣ አድልዎ መስሎ ስለሚታየኝ ነው የተገረምኩት፤ የደነገጥኩት። ረጋ ብዬ ሳስበው ግን፤ ለካ ያን ያህልም አስገራሚ አይደለም። “ኧረ ጉድ!” የሚል ሰውም አላጋጠመኝም። ደግሞም አዲስ የተፈጠረ ነገር የለም። የመንግስት ችሮታ፣ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአገራችን ባህል ነው።  የድሮ ነገስታት፣ በነሱ ፊት ከሌላው ሰው በልጦ ለታያቸው “አገልጋይ”፣ ልዩ ድጋፍ ያደርጉ ነበር። “አገር ያቀና”፣ “በታማኝነት ያገለገለ”፣ “በትውልድ ሃረጉ የከበረ”፣ “በእምነቱ የፀና” … በሚሉ የተለያዩ ሰበቦች መሬት ይሰጡታል፤ መተዳደሪያ ገቢ የሚያገኝበት ግዛት ይሸልሙታል። እንደፈቃዳቸውም፣ ላሰኛቸውና ስሜታቸውን ለነካው ሰው ወይም ተወዳጅነትን ያስገኛል ብለው ሲያስቡ ለመንገደኛ ሁሉ ምፅዋት ለመስጠት እጃቸውን ይዘረጋሉ። አልያም፣ “ስጠው” ብለው የግምጃ ቤት ተቆጣጣሪውን ያዝዙታል። አልያማ ንጉስነታቸውና መንግስትነታቸው ምኑ ላይ ነው?  በእርግጥ ነገሥታት መሬት ጠፍጥፈው አይሰሩም። ማሳ አርሰውና ብረት ቀጥቅጠው መተዳደሪያ ገቢ አያመርቱም። ግን ችግር የለውም። ያው፤ ከአንዱ ዜጋ መሬት ነጥቀው ለሌላው ይሰጣሉ። ዜጎችን እያስገበረ መተዳደሪያ ገቢ እንዲያገኝ፣ ከወንዙ ማዶና ከተራራው ወዲህ ያለውን ግዛት ሰጥቼሃለሁ ይሉታል። ትንሽ ቆንጥረው ለተወሰኑ ዜጎች በምፅዋት ያከፋፍላሉ። “ለተ