ተቃዋሚዎች የአየር ሰአት ድልድሉ ፍትሃዊ አይደለም አሉ
የአካባቢና ማሟያ ምርጫ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ራሳቸውን ለመራጩ ህዝብ እንዲያስተዋውቁ በሚል በምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተደለደለው የቴሌቪዥንና የሚዲያ የአየር ሰአት ፍትሃዊ አለመሆኑን ፓርቲዎች ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ግንባር (ኢፌዲሃግ) እና የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራሮች እንደሚሉት፤ ለኢህአዴግ የተሰጠው የቴሌቪዥን የአየር ሰአት በአጠቃላይ 210 ደቂቃ ሲሆን ለእያንዳንዱ ተቃዋሚ ፓርቲ በኢቲቪ 1 እና ኢቲቪ 2 በእያንዳንዳቸው 10 ደቂቃ ብቻ የተሰጠ ሲሆን ይሄም ገዥው ፓርቲ በተቆጣጠረው ሚዲያ ሰፊ የአየር ሽፋን ማግኘቱን እንደሚያመለክት ገልፀዋል፡፡ የአየር ሰአት ድልድሉ በተለይ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቧቸው እጩዎች ብዛት እና በ2002 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ፓርቲዎቹ ባገኙት የፓርላማ ወንበር መሆኑ የድልድሉን ፍትሃዊ አለመሆን ያጐላዋል ያሉት አመራሮቹ፤ እነዚህን መስፈርቶች ብቻ መመዘኛ ከማድረግ ይልቅ ሌሎች የዲሞክራሲ ሂደቱን ሊደግፉ የሚያስችሉ አማራጭ መስፈርቶችም ሊካተቱበት ይገባ ነበር ብለዋል፡፡ ፓርቲያቸው የአየር ሰአት ድልድሉ ፍትሃዊ ነው ብሎ ባያምንም ላለመግባባት መግባባት የሚለውን መርህ በማንገብ አብሮ በሰላምና በመግባባት መስራት የፓርቲያቸው ተቀዳሚ አላማ በመሆኑ እንደተቀበሉት የተናገሩት የኢራፓ ሊ/መንበር አቶ ተሻለ ሰብሮ፤ ለእያንዳንዱ ፓርቲ 10 ደቂቃ ብቻ በቴሌቪዥን መሰጠቱ፣ በተቃራኒው ለኢህአዴግ 210 ደቂቃ መመደቡና የ2002 ምርጫ ውጤትንና የእጩ ብዛትን እንደመስፈርት መውሰዱ የአየር ሰዓት ድልድሉ ፍትሃዊ አለመሆኑን ይጠቁማል ብለዋል፡፡ ኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፤ ለድልድሉ የቀረበው ደቂቃ ለፓርቲያቸው ምንም ጥ